1
የያዕቆብ መልእክት 3:17
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሚገኘው ጥበብ በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፥ ደግ፥ ታዛዥ፥ ምሕረት አድራጊ፥ ጥሩ ፍሬ የሞላበት፥ አድልዎና ግብዝነት የሌለበት ነው።
Compare
Explore የያዕቆብ መልእክት 3:17
2
የያዕቆብ መልእክት 3:13
ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ ሰው ማን ነው? በጥበብና በትሕትና የፈጸመውን ሥራ በመልካም አኗኗሩ ያሳይ።
Explore የያዕቆብ መልእክት 3:13
3
የያዕቆብ መልእክት 3:18
ሰላም ወዳድ ሰዎች ሰላምን ዘርተው የጽድቅን ፍሬ ይሰበስባሉ።
Explore የያዕቆብ መልእክት 3:18
4
የያዕቆብ መልእክት 3:16
ቅናትና ራስ ወዳድነት ባሉበት ስፍራ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ ይኖራሉ።
Explore የያዕቆብ መልእክት 3:16
5
የያዕቆብ መልእክት 3:9-10
በእርስዋ አባታችንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፤ እንዲሁም በእርስዋ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን። ከአንድ አፍ ምስጋናና ርግማን ይወጣሉ፤ ወንድሞቼ ሆይ! ይህ ሊሆን አይገባም።
Explore የያዕቆብ መልእክት 3:9-10
6
የያዕቆብ መልእክት 3:6
ምላስም እንደ እሳት ናት፤ ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ ክፉ ዓለም ናት፤ አካላችንን ትበክላለች፤ ከገሃነም እንደሚወጣ እሳትም የኑሮአችንን ሂደት ሁሉ ታቃጥላለች።
Explore የያዕቆብ መልእክት 3:6
7
የያዕቆብ መልእክት 3:8
ነገር ግን ምላስን ሊገራ የሚችል ማንም የለም፤ የሚገድል መርዝ የሞላባትና ዕረፍት የሌላት ክፉ ነገር ናት።
Explore የያዕቆብ መልእክት 3:8
8
የያዕቆብ መልእክት 3:1
ወንድሞቼ ሆይ! እኛ አስተማሪዎች የሆንን የባሰ ፍርድ እንደምንቀበል ታውቃላችሁና ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ።
Explore የያዕቆብ መልእክት 3:1
Home
Bible
Plans
Videos