1
የዮሐንስ ራእይ 9:20-21
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
በእነዚህ መቅሠፍቶች ከሞት የተረፉት የሰው ዘር ከእጃቸው ሥራ ተመልሰው ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትንና ከወርቅ፥ ከብር፥ ከናስ፥ ከድንጋይና ከእንጨት የተሠሩ ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ የማይችሉትን ጣዖቶች ማምለክንም አልተዉም። እንዲሁም ከነፍሰ ገዳይነታቸው፥ ከሟርታቸው፥ ከሴሰኛነታቸው፥ ከሌብነታቸውም ንስሓ አልገቡም።
Compare
Explore የዮሐንስ ራእይ 9:20-21
2
የዮሐንስ ራእይ 9:3-4
ከጢሱም ውስጥ አንበጣዎች በምድር ላይ ወጡ፤ የምድር ጊንጦችን ኀይል የመሰለ ኀይል ተሰጣቸው፤ የምድርን ሣር ሆነ ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተነገራቸው፤ መጒዳት ያለባቸው ግን በግንባራቸው ላይ የእግዚአብሔር ማኅተም የሌለባቸውን ሰዎች ብቻ ነበር።
Explore የዮሐንስ ራእይ 9:3-4
3
የዮሐንስ ራእይ 9:1
አምስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እነሆ፥ ከሰማይ ወደ ምድር የወደቀ አንድ ኮከብ አየሁ፤ የጥልቁ ጒድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 9:1
4
የዮሐንስ ራእይ 9:5
እነርሱንም ቢሆን አምስት ወር ለማሠቃየት እንጂ ለመግደል ፈቃድ አልተሰጣቸውም፤ አንበጣዎቹ የደረሰባቸው ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ሲነድፍ እንደሚሰማው ዐይነት ያለ ነው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 9:5
5
የዮሐንስ ራእይ 9:11
ንጉሥም ነበራቸው፤ እርሱ የጥልቁ ጒድጓድ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን፥ በግሪክ አጶልዮን ይባላል፤
Explore የዮሐንስ ራእይ 9:11
Home
Bible
Plans
Videos