1
የዮሐንስ ራእይ 8:1
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
በጉ ሰባተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ እኩል ሰዓት ያኽል በሰማይ ዝምታ ሆነ፤
Compare
Explore የዮሐንስ ራእይ 8:1
2
የዮሐንስ ራእይ 8:7
የመጀመሪያው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በረዶና ደም የተቀላቀለበት እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድር ሢሶ ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሢሶ ተቃጠለ፤ የለመለመ ሣርም ሁሉ ተቃጠለ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 8:7
3
የዮሐንስ ራእይ 8:13
ከዚህ በኋላ ስመለከት አንድ ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ “የቀሩት ሦስቱ መላእክት የእምቢልታቸውን ድምፅ በሚያሰሙበት ጊዜ በምድር ላይ ለሚኖሩ ሰዎች ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!” እያለ ሲጮኽ ሰማሁ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 8:13
4
የዮሐንስ ራእይ 8:8
ሁለተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ትልቅ ተራራ የሚመስል ነገር እየነደደ ወደ ባሕር ተጣለ፤ የባሕር ሢሶው ደም ሆነ፤
Explore የዮሐንስ ራእይ 8:8
5
የዮሐንስ ራእይ 8:10-11
ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦ የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ የወደቀውም በወንዞች ሢሶና በውሃ ምንጮች ላይ ነው። የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል፤ የውሃው አንድ ሦስተኛ መራራ ሆነ፤ መራራ በሆነውም ውሃ ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 8:10-11
6
የዮሐንስ ራእይ 8:12
አራተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፥ የጨረቃ አንድ ሦስተኛ፥ የኮከቦች አንድ ሦስተኛ ተመታ፤ ስለዚህ የእነርሱ አንድ ሦስተኛቸው ጨለመ፤ በዚህ ዐይነት የቀን አንድ ሦስተኛና የሌሊት አንድ ሦስተኛ ያለ ብርሃን ሆነ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 8:12
Home
Bible
Plans
Videos