1
ወደ ሮም ሰዎች 7:25
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለሚያድነኝ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! እንግዲህ እኔ በአእምሮዬ፥ ለእግዚአብሔር ሕግ ተገዢ ስሆን በሥጋ ባሕርዬ ለኃጢአት ሕግ ተገዢ ሆኜአለሁ።
Compare
Explore ወደ ሮም ሰዎች 7:25
2
ወደ ሮም ሰዎች 7:18
በእኔ ወይም በእኔ ሥጋዊ ባሕርይ ምንም መልካም ነገር እንደሌለ ዐውቃለሁ፤ መልካም ነገርን የማድረግ ፍላጎት ቢኖረኝም እንኳ ያን መልካም ነገር ለማድረግ ችሎታ የለኝም።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 7:18
3
ወደ ሮም ሰዎች 7:19
ማድረግ የምፈልገውን መልካም ነገርን አላደርግም፤ ዳሩ ግን የማልፈልገውን ክፉ ነገር አደርጋለሁ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 7:19
4
ወደ ሮም ሰዎች 7:20
ማድረግ የማልፈልገውን ክፉ ነገር የማደርግ ከሆንኩ ይህን የሚያደርገው በእኔ ውስጥ ያለው ኃጢአት ነው እንጂ እኔ አይደለሁም ማለት ነው።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 7:20
5
ወደ ሮም ሰዎች 7:21-22
ስለዚህ ሕግ በሥራ ላይ ውሎ አያለሁ፤ መልካም ነገርን ማድረግ ስፈልግ ክፉ ነገርን ለማድረግ እገደዳለሁ። ውስጣዊ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 7:21-22
6
ወደ ሮም ሰዎች 7:16
እንግዲህ እኔ የማደርገው የማልፈልገውን ነገር ከሆነ ሕግ መልካም እንደ ሆነ እመሰክራለሁ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 7:16
Home
Bible
Plans
Videos