1
ወደ ሮም ሰዎች 8:28
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እግዚአብሔርን ለሚወዱና እንደ ፈቃዱም ለተጠሩት ሰዎች እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ለበጎ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን።
Compare
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:28
2
ወደ ሮም ሰዎች 8:38-39
ስለዚህ ሞትም ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ባለሥልጣኖችም ቢሆኑ፥ አሁን ያለውም ቢሆን፥ በኋላ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኀይሎችም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ማንኛውም ፍጥረት ቢሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካገኘነው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ እርግጠኛ ነኝ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:38-39
3
ወደ ሮም ሰዎች 8:26
እንዲሁም እንዴት መጸለይ እንደሚገባን ስለማናውቅ መንፈስ ቅዱስ በድካማችን ይረዳናል፤ በቃል ሊገለጥ በማይቻል መቃተት ያማልደናል።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:26
4
ወደ ሮም ሰዎች 8:31
እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ሊቃወመን ይችላል?
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:31
5
ወደ ሮም ሰዎች 8:1
ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚኖሩ አሁን ኲነኔ የለባቸውም።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:1
6
ወደ ሮም ሰዎች 8:6
ሥጋዊ ነገርን ማሰብ ሞትን ያመጣል፤ መንፈሳዊ ነገርን ማሰብ ግን ሕይወትንና ሰላምን ይሰጣል።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:6
7
ወደ ሮም ሰዎች 8:37
እንግዲህ በወደደን በክርስቶስ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ድል በመንሣት ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:37
8
ወደ ሮም ሰዎች 8:18
የአሁኑ ጊዜ መከራ ወደፊት ለእኛ ከሚገለጥልን ክብር ጋር ቢመዛዘን በምንም ሊተካከል እንደማይችል አድርጌ እቈጥረዋለሁ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:18
9
ወደ ሮም ሰዎች 8:35
ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል ማነው? ችግር ወይስ መከራ? ስደት፥ ወይስ ራብ? ወይስ ራቊትነት፥ ወይስ አደጋ? ወይስ ሰይፍ?
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:35
10
ወደ ሮም ሰዎች 8:27
የሰውን ልብ የሚመረምር አምላክ የመንፈስ ቅዱስ ሐሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፤ መንፈስ ቅዱስ ስለ ምእመናን የሚያማልደው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ነው።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:27
11
ወደ ሮም ሰዎች 8:14
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:14
12
ወደ ሮም ሰዎች 8:5
በሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ ሥጋዊ ነገርን፥ በመንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን መንፈሳዊ ነገርን ያስባሉ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:5
13
ወደ ሮም ሰዎች 8:32
እግዚአብሔር ለአንድ ልጁ ሳይራራ ስለ እኛ አሳልፎ ከሰጠው እንዴት ከልጁ ጋር ሁሉን ነገር በነጻ አይሰጠንም?
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:32
14
ወደ ሮም ሰዎች 8:16-17
የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኛ መንፈስ ጋር ሆኖ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ለእኛ ይመሰክራል። እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን የእርሱ ወራሾች ነን፤ ከክርስቶስም ጋር እንወርሳለን፤ አሁን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች ብንሆን በኋላ የክብሩ ተካፋዮች እንሆናለን።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:16-17
15
ወደ ሮም ሰዎች 8:7
ሥጋዊ ነገርን የሚያስብ ሰው ለእግዚአብሔር ሕግ ስለማይታዘዝና መታዘዝም ስለማይችል የእግዚአብሔር ጠላት ነው።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:7
16
ወደ ሮም ሰዎች 8:19
ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በታላቅ ናፍቆት ይጠባበቃል።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:19
17
ወደ ሮም ሰዎች 8:22
ፍጥረት ሁሉ በአንድ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ በምጥ ጭንቀት ተይዞ በመቃተት ላይ መኖሩን እናውቃለን።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 8:22
Home
Bible
Plans
Videos