1
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:25-26
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ “ይህ ጽዋ በደሜ የሚመሰረት አዲስ ኪዳን ነው፤ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ። ይህን ኅብስት በምትበሉበትና ይህንም ጽዋ በምትጠጡበት ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁ።
Compare
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:25-26
2
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:23-24
እኔ ከጌታ ተቀብያለሁና፤ ለእናንተ ደግሞ ያስተላለፍኩላችሁ ይህ ነው፦ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት ኅብስትን አንሥቶ፤ አመሰገነ ቆርሶም “እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:23-24
3
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:28-29
ሰው ግን ራሱን ይመርምር፤ እንዲሁም ከኅብስቱ ይብላ፤ ከጽዋውም ይጠጣ፤ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላል፤ ይጠጣልም።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:28-29
4
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:27
ስለዚህ ያልተገባ ሆኖ ሳለ ይህን ኅብስት የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:27
5
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:1
እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:1
Home
Bible
Plans
Videos