1
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:7
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ለእያንዳንዱ የመንፈስን መገለጥ የሚሰጠው ለጥቅም ነው።
Compare
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:7
2
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:27
እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የአካሉ ክፍሎች ናችሁ።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:27
3
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:26
አንድም አካል ቢሠቃይ የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሠቃያሉ፤ አንድ አካልም ቢከበር የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:26
4
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:8-10
ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋል፤ ለሌላውም ያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፤ በዚያው መንፈስ ለአንዱ እምነት ይሰጠዋል፤ ለሌላው የመፈወስ ስጦታን በዚያው አንድ መንፈስ ይሰጠዋል፤ ለሌላው ተአምራትን የማድረግ ኃይል ይሰጠዋል፤ ለሌላው ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱ መናፍስትን መለየት፥ ለሌላው በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለሌላውም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:8-10
5
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:11
ይህን ሁሉ ግን አንዱና ያው መንፈስ ያደርጋል፤ እንደፈቃዱም ለእያንዳንዱ ሰው ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:11
6
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:25
ይህም በአካል ክፍሎች መካከል መለያየት ሳይኖር እርስ በርሳቸው እንዲተሳሰቡ ነው።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:25
7
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:4-6
ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉ፤ መንፈስ ግን አንድ ነው፤ ጌታም አንድ ሲሆን፤ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችም አሉ፤ አሠራሮችም ልዩ ልዩ አሉ፤ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ ግን አንዱ እግዚአብሔር ነው።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:4-6
8
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:28
እግዚአብሔርም አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት የሚያደርጉትን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ስጦታ ያላቸውን፥ ሰዎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፥ አስተዳዳሪዎችንና በተለያዩ ልሳኖች የሚናገሩትን ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ሰይሟል።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:28
9
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:14
አካል ብዙ የአካል ክፍሎች እንጂ አንድ የአካል ክፍል አይደለምና።
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:14
10
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:22
ነገር ግን ደካሞች የሚመስሉ የአካል ክፍሎች ይልቁን የሚያስፈልጉ ናቸው፤
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:22
11
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:17-19
አካል ሁሉ ዐይን ቢሆን መስማት ወዴት በተገኘ? ሁሉም መስማት ቢሆን ማሽተት ወዴት በተገኘ? አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ የአካል ክፍሎችን እያንዳንዳቸው በአካል አድርጎአል። ሁሉም አንድ የአካል ክፍል ቢሆንስ አካል ወዴት በሆነ?
Explore 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:17-19
Home
Bible
Plans
Videos