1
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:18
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ስለዚህ የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን እንመልከት፥ ምክንያቱም የሚታየው ጊዜያዊ ነው፤ የማይታየው ግን ዘላለማዊ ነው።
Compare
Explore 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:18
2
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:16-17
ስለዚህ አንታክትም፤ ውጫዊው ሰውነታችን እየመነመነ ቢሄድ እንኳን፥ ውስጣዊው ሰውነታችን በየዕለቱ ይታደሳል። ቀላል የሆነው ጊዜያዊ መከራችን ከመመዘኛዎች ሁሉ ለሚያልፈው ለዘላለማዊ ክብር ያዘጋጀናል።
Explore 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:16-17
3
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:8-9
ከየአቅጣጫው መከራን እንቀበላለን እንጂ አንጨነቅም፤ ግራ እንጋባለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፤ እንሰደዳለን እንጂ አንተውም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤
Explore 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:8-9
4
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:7
ነገር ግን ይህ ልዩ ኃይል የእግዚአብሄር መሆኑንና ከእኛ አለመመጣቱን ግልጽ ለማድረግ፥ ይህ ሀብት በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤
Explore 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:7
5
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:4
እንደ እነርሱ ከሆነ የማያምኑ ሰዎችን ልቦና፥ የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ አሳውሯል።
Explore 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:4
6
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:6
በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት እንዲሰጥ ብርሃን በልባችን ውስጥ ያበራ፥ “በጨለማ ብርሃን ይብራ፤” ያለው እግዚአብሔር ነው።
Explore 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:6
Home
Bible
Plans
Videos