1
ትንቢተ ኢሳይያስ 41:10
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳሀለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 41:10
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 41:13
እኔ አምላክህ ጌታ ነኝ፦ “አትፍራ፥ እረዳሃለሁ” ብዬ ቀኝህን የያዝኩ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 41:13
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 41:11
እነሆ፥ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ይዋረዳሉም፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፥ ይጠፋሉም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 41:11
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 41:9
አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና፦ “አንተ አገልጋዬ ነህ፥ መርጬሃለሁ፥ አልጥልህም!” ያልሁህ፥
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 41:9
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 41:12
የሚጣሉህንም ትፈልጋቸዋለህ አታገኛቸውምም፥ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 41:12
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 41:14
አንተ ትል ያዕቆብ፥ ታናሽ እስራኤል ሆይ፥ አትፍራ፤ እረዳሃለሁ፥ ይላል ጌታ፥ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 41:14
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 41:8
አገልጋዬ እስራኤል፥ የመረጥኩህ ያዕቆብ፥ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፥
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 41:8
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 41:18
በወናዎቹ ኮረብቶች ላይ ወንዞችን፥ በሸለቆዎችም መካከል ምንጮችን እከፍታለሁ፤ ምድረ በዳውን ለውኃ ማከማቻ፥ የጥማትንም ምድር ለውሃ መፍለቂያ አደርጋለሁ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 41:18
9
ትንቢተ ኢሳይያስ 41:17
ድሆችና ምስኪኖችም ውኃ ይሻሉ አያገኙምም፥ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ ጌታ እሰማቸዋለሁ፥ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 41:17
10
ትንቢተ ኢሳይያስ 41:4
ይህን የሠራና ያደረገ፥ ትውልድንም ከጥንት የጠራው ማን ነው? እኔ ጌታ፥ መጀመሪያም እስከ መጨረሻውም የምኖር፥ እኔ ነኝ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 41:4
11
ትንቢተ ኢሳይያስ 41:19-20
በምድረ በዳ፤ ዝግባን፤ ግራርን፤ ባርሰነትንና ወይራን አበቅላለሁ፤ በበረሃ፤ ጥድን፤ አስታንና ሸውሸዌን በአንድነት እተክላለሁ። ስለዚህ የጌታ እጅ ይህን እንዳደረገ፥ የእስራኤል ቅዱስ እንደፈጠረው፥ ሰዎች እንዲያዩና እንዲያውቁ፥ በአንድነት እንዲገነዘቡ፤ እንዲያስተውሉም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 41:19-20
Home
Bible
Plans
Videos