1
የዮሐንስ ራእይ 8:1
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ለግማሽ ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ።
Compare
Explore የዮሐንስ ራእይ 8:1
2
የዮሐንስ ራእይ 8:7
የፊተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ፤ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 8:7
3
የዮሐንስ ራእይ 8:13
አየሁም፤ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “የቀሩት ሦስቱ መላእክት መለከትን በሚነፋበት ጊዜ ከሚቀረው ድምፅ የተነሣ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!”
Explore የዮሐንስ ራእይ 8:13
4
የዮሐንስ ራእይ 8:8
ሁለተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በእሳት የሚቃጠል ታላቅ ተራራን የሚመስል ነገር በባሕር ተጣለ፤ የባሕርም ሲሶው ደም ሆነ፤
Explore የዮሐንስ ራእይ 8:8
5
የዮሐንስ ራእይ 8:10-11
ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ በወንዞችና በውሃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ። የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል፤ የውሃውም ሲሶ መራራ ሆነ፤ መራራም ስለተደረገ በውሃው ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 8:10-11
6
የዮሐንስ ራእይ 8:12
አራተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ፤ የእነዚህ ሲሶ ይጨልም ዘንድ፥ የቀንና የሌሊት ሲሶው እንዳያበራ ተከለከለ።
Explore የዮሐንስ ራእይ 8:12
Home
Bible
Plans
Videos