1
የዮሐንስ ራእይ 9:20-21
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ስለ እጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤ ለአጋንንትና ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶችም መስገድን አልተዉም። ስለ መግደላቸውም ቢሆን ወይም ስለ አስማታቸው ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሓ አልገቡም።
Compare
Explore የዮሐንስ ራእይ 9:20-21
2
የዮሐንስ ራእይ 9:3-4
ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፤ የምድርም ጊንጦች እንዳላቸው ሥልጣን ዓይነት ሥልጣን ተሰጣቸው። የእግዚአብሔርም ማኅተም በግምባራቸው ከሌለባቸው ሰዎች በቀር በምድር ያለውን ሣር ቢሆንም ወይም ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተነገራቸው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 9:3-4
3
የዮሐንስ ራእይ 9:1
አምስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ከሰማይም ወደ ምድር ወድቆ የነበረ ኮከብ አየሁ፤ የጥልቁም ጉድጓድ መክፈቻ ተሰጠው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 9:1
4
የዮሐንስ ራእይ 9:5
ለአምስትም ወር እንዲያሰቃዩአቸው እንጂ እንዲገድሉአቸው አልተፈቀደላቸውም፤ እነርሱም የሚያደርሱት ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ሲነድፍ እንደሚያደርሰው ስቃይ ዓይነት ነው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 9:5
5
የዮሐንስ ራእይ 9:11
ንጉሥም ነበራቸው፤ እርሱም የጥልቁ ጉድጓድ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን በግሪክም አጶልዮን ነው።
Explore የዮሐንስ ራእይ 9:11
Home
Bible
Plans
Videos