1
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:29
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ለደካሞች ኀይልን ይሰጣል፤ መከራ የሚቀበሉትንም አያሳዝናቸውም።
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:29
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:30-31
ብላቴኖች ይራባሉ፤ ጐልማሶች ይታክታሉ፤ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይዝላሉ። እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉና የሚታገሡ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱምም፤ ይሄዳሉ፤ አይራቡምም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:30-31
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:28
አሁንም አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ፥ የምድርንም ዳርቻ የፈጠረ አምላክ ነው፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ ማስተዋሉም አይመረመርም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:28
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:3
የዐዋጅ ነጋሪ ቃል በምድረ በዳ፥ “የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ፤ ለአምላካችንም ጎዳና በበረሃ አስተካክሉ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:3
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:8
ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ የአምላካችን ቃል ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል።”
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:8
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:5
የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጥ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ የእግዚአብሔርን ትድግና ይይ፤ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአልና።”
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:5
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:4
ሸለቆው ሁሉ ይሙላ፤ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፤ ጠማማውም ይቅና፤ ሰርጓጕጡም ሜዳ ይሁን፤
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:4
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:11
መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፤ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፤ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:11
9
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:26
ዐይናችሁን ወደ ሰማይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ ይህን ሁሉ የፈጠረ ማን ነው? ከዋክብትንም በሙሉ የሚቈጥራቸው እርሱ ነው፤ በየጊዜያቸው ያመጣቸዋል፤ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በክብሩ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:26
10
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:22
እርሱ የምድርን ክበብ ያጸናል፤ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው፥ እንደ ድንኳንም ለመኖሪያ የሚዘረጋቸው፤
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:22
11
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:2
ካህናት ሆይ፥ ለኢየሩሳሌም ወደ ልቧ የሚገባ ነገርን ተናገሩ፤ ውርደቷ እንደ ተፈጸመ፥ ኀጢአቷም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች አጽናኑአት።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:2
12
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:6-7
“ጩኽ” የሚል ሰው ቃል፤ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ። “ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፤ የሰውም ክብሩ ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነው። የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:6-7
13
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:10
እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር በኀይሉ ይመጣል፤ በክንዱም ይገዛል፤ እነሆ፥ ዋጋው ከእርሱ ጋር ሥራውም በፊቱ ነው።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:10
14
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:1
አጽናኑ፤ ሕዝቤን አጽናኑ፤ ይላል እግዚአብሔር፤
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:1
15
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:12-14
ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝሩ የለካ፥ ምድርንም ሁሉ ሰብስቦ በእጁ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን፥ ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው? የእግዚአብሔርን ሕሊና ያወቀ ወይስ አማካሪ ሆኖ ያማከረው ማን ነው? ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? ፍርድንስ ማን አስተማረው? የጥበብንስ መንገድ ማን አሳየው?
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:12-14
Home
Bible
Plans
Videos