1
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:17-18
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም፤ በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ነው እንጂ መብልና መጠጥ አይደለምና። እንዲህ አድርጎ ለክርስቶስ የሚገዛ ግን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና በሰውም ዘንድ የተመረጠ ነው።
Compare
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 14:17-18
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:8
በሕይወት ብንኖርም ለእግዚአብሔር እንኖራለን፤ ብንሞትም ለእግዚአብሔር እንሞታለን፤ እንግዲህ በሕይወት ብንኖርም ብንሞትም ለእግዚአብሔር ነን።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 14:8
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:19
አሁንም ወንድማችን ይታነጽ ዘንድ ሰላምን እንከተላት።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 14:19
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:13
እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በርሳችን አንነቃቀፍ፤ ይልቁንም ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖር ይህን ዐስቡ።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 14:13
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:11-12
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአልና፥ “እኔ ሕያው ነኝ፤ ጕልበትም ሁሉ ለእኔ ይሰግዳል፤ አንደበትም ሁሉ ለእኔ ይገዛል።” እነሆ፥ ሁላችን በእግዚአብሔር ዘንድ እንደምንመረመር ታወቀ።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 14:11-12
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:1
እምነቱ ደካማ የሆነውን ሰው ታገሡት፤ በዐሳቡም አትፍረዱ።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 14:1
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 14:4
እንግዲህ የሌላውን ሎሌ የምትነቅፍ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለጌታው ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያነሣው ይችላልና ይቆማል።
Explore ወደ ሮሜ ሰዎች 14:4
Home
Bible
Plans
Videos