1
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:29
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
ለደካማ ኃይልን ይሰጣል ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።
Compare
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:29
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:30-31
ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፥ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፥ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፥ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፥ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:30-31
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:28
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፥ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:28
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:3
የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጎዳና በበረሀ አስተካክሉ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:3
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:8
ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ ያምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:8
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:5
የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:5
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:4
ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፥ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፥
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:4
8
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:11
መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፥ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፥ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:11
9
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:26
ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፥ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፥ በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:26
10
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:22
እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፥ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፥ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:22
11
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:2
ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፥ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርስዋ ጩኹ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:2
12
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:6-7
ጩኽ የሚል ሰው ቃል፥ ምን ብዬ ልጩኽ? አልሁ። ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው። የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፥ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:6-7
13
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:10
እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይመጣል ክንዱም ስለ እርሱ ይገዛል፥ እነሆ፥ ዋጋው ከእርሱ ጋር ደመወዙም በፊቱ ነው።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:10
14
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:1
አጽናኑ፥ ሕዝቤን አጽናኑ ይላል አምላካችሁ።
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:1
15
ትንቢተ ኢሳይያስ 40:12-14
ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝር የለካ፥ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው? የእግዚአብሔርም መንፈስ ያዘዘ፥ ወይስ አማካሪ ሆኖ ያስተማረው ማን ነው? ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? የፍርድንም መንገድ ማን አስተማረው? እውቀትንስ ማን አስተማረው? የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው?
Explore ትንቢተ ኢሳይያስ 40:12-14
Home
Bible
Plans
Videos