1 ተሰሎንቄ 1
1
1ከጳውሎስ፣ ከሲላስና#1፥1 ግሪኩ ሲልዋኑስ ይላል። ከጢሞቴዎስ፤
በእግዚአብሔር አብና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሆኑት ለተሰሎንቄ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን፤
ከእግዚአብሔር አብ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን#1፥1 አንዳንድ ቅጆች ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው የላቸውም።።
ስለ ተሰሎንቄ ሰዎች እምነት የቀረበ ምስጋና
2በጸሎታችን እያስታወስናችሁ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ስለ ሁላችሁ እናመሰግናለን። 3ከእምነት የሆነውን ሥራችሁን፣ ከፍቅር የመነጨውን ድካማችሁንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ተስፋ የተገኘውን ጽናታችሁን በአምላካችንና በአባታችን ፊት ዘወትር እናስባለን።
4በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ ወንድሞች#1፥4 ወንድሞች የሚለው የግሪኩ ቃል ወንዶችን ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቤተ ሰብ አካል በመሆናቸው ያመኑትን ወንዶችንና ሴቶችንም ያመለክታል፤ ከዚህ ቍጥር ውጪ በ2፥1፣9፣14፣17፤ 3፥7፤ 4፥1፣10፣13፤ 5፥1፣4፣12፣14፣25፣27 ላይ እናገኘዋለን። ሆይ፣ እርሱ እንደ መረጣችሁ እናውቃለን፤ 5ምክንያቱም ወንጌላችን ወደ እናንተ የመጣው በኀይልና በመንፈስ ቅዱስ፣ በብዙም መረዳት እንጂ በቃል ብቻ አይደለም። ደግሞ ስለ እናንተ ስንል በመካከላችሁ እንዴት እንደ ኖርን ታውቃላችሁ። 6እናንተ እኛንና ጌታን መስላችኋል፤ ምንም እንኳ ብርቱ መከራ ቢደርስባችሁም፣ ቃሉን በመንፈስ ቅዱስ ደስታ ተቀብላችኋል። 7ከዚህም የተነሣ በመቄዶንያና በአካይያ ለሚገኙ ምእመናን መልካም ምሳሌ ሆናችኋል። 8የጌታ ቃል ከእናንተ ወጥቶ በመቄዶንያና በአካይያ መሰማቱ ብቻ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ያላችሁ እምነት በሁሉ ቦታ ታውቋል፤ ስለዚህ እኛ በዚህ ጕዳይ ላይ ምንም መናገር አያስፈልገንም፤ 9በእንዴት ያለ አቀባበል እንደ ተቀበላችሁንና ሕያውና እውነተኛ የሆነውን አምላክ ለማገልገል ከጣዖታት ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደ ተመለሳችሁ እነርሱ ራሳቸው ይናገራሉ፤ 10ደግሞም ከሙታን ያስነሣውንና ከሰማይ የሚመጣውን ልጁን፣ ከሚመጣውም ቍጣ የሚያድነንን ኢየሱስን እንዴት እንደምትጠባበቁ ይናገራሉ።
Currently Selected:
1 ተሰሎንቄ 1: NASV
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.