YouVersion Logo
Search Icon

ኢሳይያስ 12

12
የውዳሴ መዝሙር
1በዚያ ቀን እንዲህ ትላለህ፤
እግዚአብሔር ሆይ፤
ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤
አሁን ግን ከቍጣህ ተመለስህ፤
ደግሞም አጽናንተኸኛልና አወድስሃለሁ።
2እነሆ፣ አምላክ ድነቴ ነው፤
እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤
ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ#12፥2 ወይም ዝማሬዬ ነው፤
ድነቴም ሆኗል።”
3ከድነቴ ምንጮች
ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።
4በዚያ ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤
እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤
ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤
ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ።
5እግዚአብሔር ዘምሩ፤ ታላቅ ሥራ ሠርቷልና፤
ይህም ለዓለም ሁሉ ይታወቅ።
6የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤
በደስታም ዘምሩ፤
በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።”

Currently Selected:

ኢሳይያስ 12: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for ኢሳይያስ 12