መዝሙር 84
84
መዝሙር 84
ለመዘምራን አለቃ፤ በጊቲት#84፥0 የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ የሚያሳይ ወይም በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም። የሚዜም የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤
ማደሪያህ ምንኛ የተወደደ ነው!
2ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትናፍቃለች፤
እጅግም ትጓጓለታለች፤
ልቤና ሥጋዬም፣
ለሕያው አምላክ እልል በሉ።
3ንጉሤና አምላኬ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤
መሠዊያህ ባለበት ስፍራ፣
ድንቢጥ እንኳ መኖሪያ ቤት፣
ዋኖስም ጫጩቶቿን የምታኖርበት ጐጆ አገኘች።
4ብፁዓን ናቸው፤
በቤትህ የሚኖሩ፣
እነርሱም ለዘላለም ያመሰግኑሃል። ሴላ
5ብፁዓን ናቸው፤
አንተን ብርታታቸው ያደረጉ፣
በልባቸው የጽዮንን መንገድ የሚያስቡ፤
6በልቅሶ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ፣
የምንጭ መፍለቂያ ቦታ ያደርጉታል፤
የበልጕም ዝናብ ያረሰርሰዋል።#84፥6 ወይም ይባርከዋል
7ከኀይል ወደ ኀይል ይሸጋገራሉ፤
እያንዳንዱም በጽዮን ባለው አምላክ ፊት ይቀርባል።
8የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤
የያዕቆብ አምላክ ሆይ አድምጠኝ። ሴላ
9አምላክ ሆይ፤ ጋሻችንን#84፥9 ወይም ልዑል እይልን፤
የቀባኸውንም ተመልከት።
10በሌላ ስፍራ ሺሕ ቀን ከመኖር፣
በአደባባይህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላል፤
በክፉዎች ድንኳን ከመቀመጥ ይልቅ፣
በአምላኬ ቤት ደጅ መቆም እመርጣለሁ።
11 እግዚአብሔር አምላክ ፀሓይና ጋሻ ነውና፤
እግዚአብሔር ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤
እግዚአብሔር ያለ ነቀፋ የሚሄዱትን፣ መልካም ነገር አይነፍጋቸውም።
12የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤
በአንተ የታመነ ሰው ብፁዕ ነው።
Currently Selected:
መዝሙር 84: NASV
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.