YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙር 91

91
መዝሙር 91
1በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣
በሁሉን ቻይ አምላክ#91፥1 በዕብራይስጥ ሻዳይ ማለት ነው። ጥላ ሥር ያድራል።
2 እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣
የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።#91፥2 አንዳንድ ትርጕሞች ይላል ይላሉ።
3እርሱ ከዐዳኝ ወጥመድ፣
ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና።
4በላባዎቹ ይጋርድሃል፤
በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤
ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል።
5የሌሊትን አስደንጋጭነት፣
በቀን የሚወረወረውንም ፍላጻ አትፈራም፤
6በጨለማ የሚያደባ ቸነፈር፣
በቀትር ረፍራፊውም አያሠጋህም።
7በአጠገብህ ሺሕ፣ በቀኝህም ዐሥር ሺሕ ይወድቃል፤
ወደ አንተ ግን አይቀርብም።
8በዐይንህ ብቻ ትመለከታለህ፤
የክፉዎችንም መቀጣት ታያለህ።
9 “እግዚአብሔርን መሸሸጊያ፣”
ልዑልንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና።
10ክፉ ነገር አያገኝህም፤
መቅሠፍትም ወደ ድንኳንህ አይገባም፤
11በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣
እግርህም ከድንጋይ ጋራ እንዳይሰናከል፤
12በእጆቻቸው ያነሡህ ዘንድ፣
መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዝልሃል።
13በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤
ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
14“ወድዶኛልና እታደገዋለሁ፤
ስሜን ዐውቋልና እከልለዋለሁ።
15ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤
በመከራው ጊዜ ከርሱ ጋራ እሆናለሁ፤
አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ።
16ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤
ማዳኔንም አሳየዋለሁ።”

Currently Selected:

መዝሙር 91: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in