YouVersion Logo
Search Icon

ሮሜ 10

10
1ወንድሞች ሆይ፤ ስለ እስራኤላውያን የልቤ ምኞት፣ እግዚአብሔርንም የምለምነው እንዲድኑ ነው። 2ለእግዚአብሔር ቀናተኞች እንደ ሆኑ ስለ እነርሱ መመስከር እችላለሁና፤ ቅናታቸው ግን ከዕውቀት የተነሣ አይደለም። 3ከእግዚአብሔር የሚመጣውን ጽድቅ ስላላወቁና የራሳቸውን ጽድቅ ለመመሥረት ስለ ፈለጉ፣ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም። 4ለሚያምን ሁሉ ጽድቅ ይሆን ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።
5ሙሴ በሕግ በኩል የሆነውን ጽድቅ ሲገልጽ፣ “እነዚህን የሚፈጽም ሰው በእነርሱ ሕያው ይሆናል”#10፥5 ዘሌ 18፥5 ይላል። 6ከእምነት የሆነው ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፤ “ ‘በልብህ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል?’ አትበል”#10፥6 ዘዳ 30፥12፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ 7“ወይም ‘ወደ ጥልቁስ ማን ይወርዳል?’ አትበል”#10፥7 ዘዳ 30፥13፤ ይህም ክርስቶስን ከሙታን ለማውጣት ነው። 8ነገር ግን ምን ይላል? “ቃሉ በአጠገብህ ነው፤ በአፍህና በልብህም ውስጥ ነው፤”#10፥8 ዘዳ 30፥14 የምንሰብከውም የእምነት ቃል ይህ ነው፤ 9“ኢየሱስ ጌታ ነው” ብለህ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን፣ ትድናለህ። 10የምትጸድቀው በልብህ አምነህ ነው፤ የምትድነውም በአፍህ መስክረህ ነውና። 11መጽሐፍ እንደሚለው፣ “በርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም።”#10፥11 ኢሳ 28፥16 12በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ልዩነት የለም፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፤ የሚለምኑትንም አብዝቶ ይባርካል፤ 13“የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”#10፥13 ኢዩ 2፥32
14ታዲያ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ስለ እርሱስ ሳይሰሙ እንዴት ያምኑበታል? ሰባኪ ሳይኖር እንዴት መስማት ይችላሉ? 15ካልተላኩስ እንዴት መስበክ ይችላሉ? ይህም፣ “የምሥራችን የሚያመጡ እግሮች እንዴት ያማሩ ናቸው!”#10፥15 ኢሳ 52፥7 ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።
16ነገር ግን የሰሙት ሁሉ የምሥራቹን ቃል አልተቀበሉም፤ ኢሳይያስም፣ “ጌታ ሆይ፤ መልእክታችንን ማን አምኗል?”#10፥16 ኢሳ 53፥1 ብሏልና። 17እንግዲያስ እምነት የሚገኘው መልእክቱን ከመስማት ነው፤ መልእክቱም በክርስቶስ ቃል ነው። 18ነገር ግን አልሰሙ ይሆን? ብዬ እጠይቃለሁ፤ በርግጥ ሰምተዋል፤
“ድምፃቸው በምድር ሁሉ፣
ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ተሰማ።”#10፥18 መዝ 19፥4
19ደግሜም እጠይቃለሁ፤ እስራኤል አላስተዋሉ ይሆን? በቅድሚያ ሙሴ እንዲህ ይላል፤
“ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤
ማስተዋል በሌለው ሕዝብም አስቈጣቸዋለሁ”#10፥19 ዘዳ 32፥12
20ኢሳይያስም በድፍረት፣
“ላልፈለጉኝ ተገኘሁላቸው፤
ላልጠየቁኝም ራሴን ገለጥሁላቸው”#10፥20 ኢሳ 65፥1 ይላል።
21ስለ እስራኤል ግን፣
“ወደማይታዘዝና ዕሺ ወደማይል ሕዝብ፣
ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ”#10፥21 ኢሳ 65፥2 ይላል።

Currently Selected:

ሮሜ 10: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for ሮሜ 10