1 የጴጥሮስ መልእክት 3
3
ስለ ባልና ሚስት
1እንዲሁም እናንተ ሚስቶች! ለባሎቻችሁ ታዘዙ፤ በዚህ ዐይነት አንዳንዶች በእግዚአብሔር ቃል የማያምኑ ቢሆኑም እንኳ ያለ ቃሉ ትምህርት በሚስቶቻቸው ጠባይ ብቻ ሊሳቡ ይችሉ ይሆናል። #ኤፌ. 5፥22፤ ቆላ. 3፥18። 2ሊሳቡ የሚችሉትም ንጹሕ የሆነውንና ሰው አክባሪ የሆነውን ሕይወታችሁን ሲመለከቱ ነው። 3የእናንተ ውበት ጠጒርን በመሠራት፥ በወርቅ በማጌጥና፥ የከበረ ልብስ በመልበስ በውጪ በሚታየው ጌጥ አይሁን። #1ጢሞ. 2፥9። 4ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጭምትነት መንፈስ ያጌጠው፥ በልብ ተሰውሮ የሚገኘው፥ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን። 5በቀድሞ ጊዜ ተስፋቸውን በእግዚአብሔር ላይ የጣሉ፥ የተቀደሱ ሴቶች ያጌጡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ ለባሎቻቸውም ይታዘዙ ነበር። 6የታዘዙትም ሣራ አብርሃምን “ጌታዬ!” እያለች ትታዘዝለት እንደ ነበረው ዐይነት ነው፤ እናንተም መልካም የሆነውን ነገር ብታደርጉና አንዳች የሚያስፈራ ነገር ባያስደነግጣችሁ የእርስዋ ልጆች ናችሁ። #ዘፍ. 18፥12።
7እናንተም ባሎች! ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ከእናንተ ይልቅ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑና ከእናንተም ጋር የሕይወትን ጸጋ ስለሚወርሱ አክብሩአቸው፤ በዚህ ዐይነት ለጸሎታችሁ መሰናክል የሚሆን ነገር አይኖርም። #ኤፌ. 5፥25፤ ቆላ. 3፥19።
መልካም በማድረግ መከራን መቀበል
8በቀረውስ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ በመስማማት ኑሩ፤ የሌላውን ሰው ችግር እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁ ቊጠሩ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ደጎችና ትሑቶች ሁኑ። 9መርቁ እንጂ ክፉውን በክፉ ፈንታ፥ ስድብንም በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ እናንተ የተጠራችሁት ይህን በማድረግ በረከትን ለመውረስ ነው፤ 10ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለው፦
“ሕይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ማየት የሚፈልግ፥
ምላሱ ክፉ ነገር እንዳይናገር፥
ከንፈሮቹ ተንኰልን እንዳይናገሩ ይከልክል።
11ከክፉ ነገር ይራቅ፤ መልካምን ነገር ያድርግ፤
ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተላትም፤
12የጌታ ዐይኖች
ወደ ጻድቃን ይመለከታሉ፤
ጆሮዎቹም ጸሎታቸውን ለመስማት ተከፍተዋል፤
በክፉ አድራጊዎች ላይ ግን
ጌታ የቊጣ ፊቱን ያሳያል።” #መዝ. 34፥12-16።
13መልካም ነገር ለማድረግ ብትተጉ ጒዳት የሚያደርስባችሁ ማን ነው? 14መልካም ነገር በማድረግ መከራን ብትቀበሉ እንኳ በረከትን ታገኛላችሁ፤ የሰዎችን ዛቻ አትፍሩ፤ አትጨነቁም። #ማቴ. 5፥10፤ ኢሳ. 8፥12-13። 15ጌታ ክርስቶስን በልባችሁ አክብሩት፤ ለሕይወታችሁም ጌታ አድርጉት፤ በእናንተ ስላለውም ተስፋ ለሚጠይቃችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ ዝግጁዎች ሁኑ። 16መልሳችሁ ግን በገርነትና በአክብሮት ይሁን፤ የክርስቶስ በመሆናችሁ ባላችሁ መልካም ጠባይ ላይ ክፉ የሚናገሩ ሰዎች በክፉ ንግግራቸው እንዲያፍሩ መልካም ኅሊና ይኑራችሁ። 17የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ እናንተ ክፉ ነገርን በማድረግ መከራ ከምትቀበሉ መልካም ነገርን በማድረግ መከራ ብትቀበሉ ይሻላል። 18ክርስቶስም ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ሳለ ጽድቅ ለሌለን ለእኛ በኃጢአታችን ምክንያት በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ መከራን በመቀበል ሞቶአል፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ። 19በዚያው መንፈስ በእስር ቤት ወዳሉት ነፍሶች ሄዶ የምሥራቹን ቃል አበሠራቸው። 20እነዚህ በወህኒ ቤት የነበሩ መናፍስት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው ሳለ አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በዚያ መርከብ ውስጥ ገብተው በውሃ አማካይነት የዳኑት ቊጥራቸው ስምንት የሆነ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው። #ዘፍ. 6፥1—7፥24። 21ይህም ውሃ አሁን እናንተን የሚያድን የጥምቀት ምሳሌ ነው፤ ይህ ጥምቀት የሰውነትን ዕድፍ ማስወገድ ሳይሆን ንጹሕ ኅሊናን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ልመና ነው፤ የሚያድናችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካይነት ነው፤ 22እርሱ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ነው፤ መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ተገዝተውለታል።
Currently Selected:
1 የጴጥሮስ መልእክት 3: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: