መጽሐፈ መዝሙር 20
20
ድል ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
1በችግር ቀን እግዚአብሔር ጸሎትህን ይስማ!
የያዕቆብ አምላክም ስም ይጠብቅህ!
2ከመቅደሱ ርዳታውን ይላክልህ፤
ከጽዮን ተራራም ይደግፍህ።
3መባህን ሁሉ ይቀበልልህ፤
በመሥዋዕትህም ደስ ይበለው።
4የልብህን ምኞት ይስጥህ፤
ሐሳብህን ሁሉ ይፈጽምልህ፤
5ድል በማድረግህ እልል እንላለን፤
በአምላካችንም ስም ዓርማችንን ከፍ እናደርጋለን፤
እግዚአብሔር ልመናህን ሁሉ ይፈጽምልህ።
6እግዚአብሔር ቀብቶ ያነገሠውን እንደሚረዳ አሁን ዐውቃለሁ፤
በቀኝ እጁ ታላቅ ድልን በማቀዳጀት
ከተቀደሰው ቦታ ከሰማይ ለጸሎቱ መልስ ይሰጠዋል።
7አንዳንዶች በጦር ሠረገሎቻቸው፥
ሌሎችም በፈረሶቻቸው ይመካሉ፤
እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ኀይል
እንታመናለን።
8እነርሱ ተሰናክለው ይወድቃሉ፤
እኛ ግን እንነሣለን፤ ጸንተንም እንቆማለን።
9አምላክ ሆይ! ንጉሡን ከጠላቶቹ እጅ አድነው፤
እኛም በምንጠራህ ጊዜ ስማን።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 20: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997