መጽሐፈ መዝሙር 34
34
ስለ እግዚአብሔር ቸርነት የሚቀርብ ምስጋና
1ዘወትር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤
ምስጋናውም ዘወትር በአንደበቴ ነው። #1ሳሙ. 21፥13-15።
2በሙሉ ልቤ በእግዚአብሔር እመካለሁ፤
ትሑቶች ይህን ሰምተው ደስ ይበላቸው!
3የእግዚአብሔርን ታላቅነት ከእኔ ጋር አስታውቁ፤
በኅብረትም ስሙን እናክብር።
4የእግዚአብሔርን ርዳታ ፈለግኹ እርሱም ሰማኝ፤
ከምፈራውም ነገር ሁሉ አዳነኝ።
5ወደ እርሱ የሚመለከቱ ሁሉ ፊታቸው ይበራል፤
ፊታቸውም ከቶ በኀፍረት አይሸፈነም።
6ይህ ድኻ ሰው ተጣራ፤
እግዚአብሔርም ሰማው፤
ከችግሩም ሁሉ አዳነው።
7የእግዚአብሔር መልአክ
እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች ይጠብቃል፤
በዙሪያቸውም ሆኖ ከአደጋ ያድናቸዋል።
8የእግዚአብሔርን ደግነት እዩና ቅመሱ፤
እርሱን ከለላ ያደረገ የተባረከ ነው። #1ጴጥ. 2፥3።
9እርሱን የሚፈሩት ሁሉ ምንም ስለማያጡ
እናንተ ቅዱሳኑ እግዚአብሔርን ፍሩ
10የአንበሳ ደቦሎች ያጣሉ፤ ይራባሉም፤
እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ምንም አይጐድልባቸውም፤
መልካም ነገርም አያጡም።
11ልጆቼ ሆይ! ኑ አድምጡኝ፤
እኔም እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
12ከእናንተ መኖርንና ለብዙ ዘመንም
መልካም ነገርን ለማየት የሚመኝ ማነው?
13እንግዲያውስ መጥፎ ነገር ከማውራትና
ሐሰት ከመናገር ተቈጠቡ።
14ከክፉ ነገር ሽሹ፤
መልካም ነገርንም አድርጉ፤
ሰላምን ፈልጉአት፤ ተከተሉአትም።
15እግዚአብሔር ወደ ጻድቃን ይመለከታል፤
ጸሎታቸውንም ያደምጣል።
16ክፉ አድራጊዎችን ግን ይቃወማል፤
መታሰቢያቸውንም ከምድር ላይ ያጠፋል። #1ጴጥ. 3፥10-12።
17ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤
እርሱም ይሰማቸዋል፤
ከችግራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።
18ልባቸው ለተሰበረ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤
መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል።
19ጻድቅ ብዙ መከራ ይደርስበታል፤
እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ ያድነዋል።
20እግዚአብሔር አጥንቶቹን ስለሚጠብቅ
ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይሰበርም። #ዮሐ. 19፥36።
21ክፋት ክፉ ሰዎችን ይገድላል፤
ደጋግ ሰዎችን የሚጠሉ ሁሉ ይቀጣሉ።
22እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ሕይወት ያድናል፤
በእርሱ የተማጠኑትም ክፉ ነገር አይደርስባቸውም።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 34: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 34
34
ስለ እግዚአብሔር ቸርነት የሚቀርብ ምስጋና
1ዘወትር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤
ምስጋናውም ዘወትር በአንደበቴ ነው። #1ሳሙ. 21፥13-15።
2በሙሉ ልቤ በእግዚአብሔር እመካለሁ፤
ትሑቶች ይህን ሰምተው ደስ ይበላቸው!
3የእግዚአብሔርን ታላቅነት ከእኔ ጋር አስታውቁ፤
በኅብረትም ስሙን እናክብር።
4የእግዚአብሔርን ርዳታ ፈለግኹ እርሱም ሰማኝ፤
ከምፈራውም ነገር ሁሉ አዳነኝ።
5ወደ እርሱ የሚመለከቱ ሁሉ ፊታቸው ይበራል፤
ፊታቸውም ከቶ በኀፍረት አይሸፈነም።
6ይህ ድኻ ሰው ተጣራ፤
እግዚአብሔርም ሰማው፤
ከችግሩም ሁሉ አዳነው።
7የእግዚአብሔር መልአክ
እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች ይጠብቃል፤
በዙሪያቸውም ሆኖ ከአደጋ ያድናቸዋል።
8የእግዚአብሔርን ደግነት እዩና ቅመሱ፤
እርሱን ከለላ ያደረገ የተባረከ ነው። #1ጴጥ. 2፥3።
9እርሱን የሚፈሩት ሁሉ ምንም ስለማያጡ
እናንተ ቅዱሳኑ እግዚአብሔርን ፍሩ
10የአንበሳ ደቦሎች ያጣሉ፤ ይራባሉም፤
እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ምንም አይጐድልባቸውም፤
መልካም ነገርም አያጡም።
11ልጆቼ ሆይ! ኑ አድምጡኝ፤
እኔም እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
12ከእናንተ መኖርንና ለብዙ ዘመንም
መልካም ነገርን ለማየት የሚመኝ ማነው?
13እንግዲያውስ መጥፎ ነገር ከማውራትና
ሐሰት ከመናገር ተቈጠቡ።
14ከክፉ ነገር ሽሹ፤
መልካም ነገርንም አድርጉ፤
ሰላምን ፈልጉአት፤ ተከተሉአትም።
15እግዚአብሔር ወደ ጻድቃን ይመለከታል፤
ጸሎታቸውንም ያደምጣል።
16ክፉ አድራጊዎችን ግን ይቃወማል፤
መታሰቢያቸውንም ከምድር ላይ ያጠፋል። #1ጴጥ. 3፥10-12።
17ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤
እርሱም ይሰማቸዋል፤
ከችግራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።
18ልባቸው ለተሰበረ እግዚአብሔር ቅርብ ነው፤
መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል።
19ጻድቅ ብዙ መከራ ይደርስበታል፤
እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ ያድነዋል።
20እግዚአብሔር አጥንቶቹን ስለሚጠብቅ
ከእነርሱ አንዱ እንኳ አይሰበርም። #ዮሐ. 19፥36።
21ክፋት ክፉ ሰዎችን ይገድላል፤
ደጋግ ሰዎችን የሚጠሉ ሁሉ ይቀጣሉ።
22እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ሕይወት ያድናል፤
በእርሱ የተማጠኑትም ክፉ ነገር አይደርስባቸውም።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997