መጽሐፈ መዝሙር 35
35
የእግዚአብሔርን ርዳታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ! የሚቃወሙኝን ተቃወማቸው፤
የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው።
2ጋሻና ጥሩር ያዝ፤
መጥተህም እርዳኝ።
3በሚያሳድዱኝ ላይ ጦርና ሰይፍህን ምዘዝና
“እኔ አዳኝህ ነኝ” ብለህ አረጋግጥልኝ።
4እኔን ለመግደል የሚፈልጉ ሁሉ
ኀፍረትና ውርደት ይድረስባቸው!
በእኔ ላይ የሚያሤሩም ሁሉ
ተዋርደው ወደ ኋላቸው ይመለሱ!
5የእግዚአብሔር መልአክ ሲያሳድዳቸው፤
በነፋስ እንደሚበተን ገለባ ይሁኑ!
6የእግዚአብሔር መልአክ ሲያሳድዳቸው
መንገዳቸው ጨለማና ድጥ ይሁንባቸው!
7ያለ ምክንያት ወጥመድ በድብቅ ዘርግተውብኛል፤
እኔንም ለመያዝ ጒድጓድ ቆፍረዋል።
8ያላሰቡት ድንገተኛ ጥፋት ይድረስባቸው፤
የደበቁት ወጥመድ ይያዛቸው
በቈፈሩትም ጒድጓድ ወድቀው ይጥፉ!
9ነፍሴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፤
በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች።
10ጌታ ሆይ! ሁለመናዬ እንዲህ ብሎ ይናገራል፤
ተበዳዮችን ከበደለኛ የሚያድን፥
ድኾችንና ተጨቋኞችን ከነጣቂዎች የሚጠብቅ
እንደ አንተ ያለ ማነው?
11ክፉ ሰዎች ባልሠራሁት ወንጀል ከሰሱኝ፤
በማላውቀውም ነገር በሐሰት መሰከሩብኝ።
12እኔን ብቸኛ አድርገው
ደግን በክፉ መለሱልኝ።
13እኔ ግን እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስኩ፤
ሰውነቴንም በጾም አጐሳቈልኩ፤
ጸሎቴም መልስ ሳያገኝ ቀረ።
14ያዘንኩትም ለወዳጅ ወይም ለወንድም
የሚታዘነውን ያኽል ነው፤
እናቱ የሞተችበት ሰው የሚያዝነውን ያኽል
ራሴን ዝቅ አድርጌ አለቀስኩ።
15በተደናቀፍኩ ጊዜ ደስ ብሎአቸው ተሰባሰቡ፤
የማላውቃቸው ጋጠወጦች መጥተው
ያለማቋረጥ አላገጡብኝ።
16ክፉዎች ሰዎች እንደሚያደርጉት
እነርሱ በክፋት አፌዙብኝ፤
በእኔም ላይ ጥርሳቸውን አፋጩ።
17እግዚአብሔር ሆይ!
እስከ መቼ ድረስ ዝም ብለህ ታየኛለህ?
ከክፉ ሥራቸው አድነኝ፤
ከእነዚህ እንደ አንበሳ ጨካኝ ከሆኑ ሰዎች ታደገኝ!
18በዚያን ጊዜ በሕዝብ ጉባኤ መካከል ሆኜ አመሰግንሃለሁ፤
ብዙ ሕዝብም በተሰበሰበበት ቦታ አከብርሃለሁ።
19ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ጠላቶቼ በእኔ ምክንያት
እንዲደሰቱ አታድርግ፤
በኋላዬ ሆነው እንዲጠቃቀሱብኝም አታድርግ። #መዝ. 69፥4፤ ዮሐ. 15፥25።
20አነጋገራቸው የጠላት አነጋገር ነው፤
በሰላማዊ ሰው ላይ ተንኰልን ያቅዳሉ።
21“ይኸዋ! ይኸዋ!
እኛ ራሳችን የሠራኸውን አየን!”
እያሉ በመጮኽ ያሳጡኛል።
22እግዚአብሔር ሆይ!
አንተ ይህን ተመልክተሃል፤
ስለዚህ ጌታ ሆይ!
ዝም አትበል! ከእኔም አትራቅ!
23ጌታዬና አምላኬ ሆይ!
ተነሥተህ ተከላከልልኝ፤
ተነሥተህም ፍረድልኝ።
24እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ!
እንደ ጻድቅነትህ
በእውነት ፍረድልኝ፤
ጠላቶቼም በእኔ ላይ ደስ እንዲላቸው አታድርግ።
25“ይኸዋ የልባችን ምኞት ደረሰ!” ብለው እንዲያስቡና ወይም “እኛ አሸነፍነው!”
እንዲሉ አታድርግ።
26በእኔ መከራ ተደስተው ትኲር ብለው በንቀት
የሚመለከቱኝ ሁሉ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤
በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ሁሉ
ኀፍረትንና ውርደትን ይልበሱ።
27ድል ማድረጌ የሚያስደስታቸው ሁሉ ደስ ይበላቸው፤
“እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
ለአገልጋዩ ሁኔታዎች ሁሉ ሲሳኩለት እግዚአብሔር ደስ ይለዋል!” ይበሉ።
28አንደበቴ ቀኑን ሙሉ
ስለ ጽድቅህና ስለ ምስጋናህ ይናገራል።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 35: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 35
35
የእግዚአብሔርን ርዳታ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ! የሚቃወሙኝን ተቃወማቸው፤
የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው።
2ጋሻና ጥሩር ያዝ፤
መጥተህም እርዳኝ።
3በሚያሳድዱኝ ላይ ጦርና ሰይፍህን ምዘዝና
“እኔ አዳኝህ ነኝ” ብለህ አረጋግጥልኝ።
4እኔን ለመግደል የሚፈልጉ ሁሉ
ኀፍረትና ውርደት ይድረስባቸው!
በእኔ ላይ የሚያሤሩም ሁሉ
ተዋርደው ወደ ኋላቸው ይመለሱ!
5የእግዚአብሔር መልአክ ሲያሳድዳቸው፤
በነፋስ እንደሚበተን ገለባ ይሁኑ!
6የእግዚአብሔር መልአክ ሲያሳድዳቸው
መንገዳቸው ጨለማና ድጥ ይሁንባቸው!
7ያለ ምክንያት ወጥመድ በድብቅ ዘርግተውብኛል፤
እኔንም ለመያዝ ጒድጓድ ቆፍረዋል።
8ያላሰቡት ድንገተኛ ጥፋት ይድረስባቸው፤
የደበቁት ወጥመድ ይያዛቸው
በቈፈሩትም ጒድጓድ ወድቀው ይጥፉ!
9ነፍሴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል፤
በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች።
10ጌታ ሆይ! ሁለመናዬ እንዲህ ብሎ ይናገራል፤
ተበዳዮችን ከበደለኛ የሚያድን፥
ድኾችንና ተጨቋኞችን ከነጣቂዎች የሚጠብቅ
እንደ አንተ ያለ ማነው?
11ክፉ ሰዎች ባልሠራሁት ወንጀል ከሰሱኝ፤
በማላውቀውም ነገር በሐሰት መሰከሩብኝ።
12እኔን ብቸኛ አድርገው
ደግን በክፉ መለሱልኝ።
13እኔ ግን እነርሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስኩ፤
ሰውነቴንም በጾም አጐሳቈልኩ፤
ጸሎቴም መልስ ሳያገኝ ቀረ።
14ያዘንኩትም ለወዳጅ ወይም ለወንድም
የሚታዘነውን ያኽል ነው፤
እናቱ የሞተችበት ሰው የሚያዝነውን ያኽል
ራሴን ዝቅ አድርጌ አለቀስኩ።
15በተደናቀፍኩ ጊዜ ደስ ብሎአቸው ተሰባሰቡ፤
የማላውቃቸው ጋጠወጦች መጥተው
ያለማቋረጥ አላገጡብኝ።
16ክፉዎች ሰዎች እንደሚያደርጉት
እነርሱ በክፋት አፌዙብኝ፤
በእኔም ላይ ጥርሳቸውን አፋጩ።
17እግዚአብሔር ሆይ!
እስከ መቼ ድረስ ዝም ብለህ ታየኛለህ?
ከክፉ ሥራቸው አድነኝ፤
ከእነዚህ እንደ አንበሳ ጨካኝ ከሆኑ ሰዎች ታደገኝ!
18በዚያን ጊዜ በሕዝብ ጉባኤ መካከል ሆኜ አመሰግንሃለሁ፤
ብዙ ሕዝብም በተሰበሰበበት ቦታ አከብርሃለሁ።
19ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ጠላቶቼ በእኔ ምክንያት
እንዲደሰቱ አታድርግ፤
በኋላዬ ሆነው እንዲጠቃቀሱብኝም አታድርግ። #መዝ. 69፥4፤ ዮሐ. 15፥25።
20አነጋገራቸው የጠላት አነጋገር ነው፤
በሰላማዊ ሰው ላይ ተንኰልን ያቅዳሉ።
21“ይኸዋ! ይኸዋ!
እኛ ራሳችን የሠራኸውን አየን!”
እያሉ በመጮኽ ያሳጡኛል።
22እግዚአብሔር ሆይ!
አንተ ይህን ተመልክተሃል፤
ስለዚህ ጌታ ሆይ!
ዝም አትበል! ከእኔም አትራቅ!
23ጌታዬና አምላኬ ሆይ!
ተነሥተህ ተከላከልልኝ፤
ተነሥተህም ፍረድልኝ።
24እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ!
እንደ ጻድቅነትህ
በእውነት ፍረድልኝ፤
ጠላቶቼም በእኔ ላይ ደስ እንዲላቸው አታድርግ።
25“ይኸዋ የልባችን ምኞት ደረሰ!” ብለው እንዲያስቡና ወይም “እኛ አሸነፍነው!”
እንዲሉ አታድርግ።
26በእኔ መከራ ተደስተው ትኲር ብለው በንቀት
የሚመለከቱኝ ሁሉ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤
በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ሁሉ
ኀፍረትንና ውርደትን ይልበሱ።
27ድል ማድረጌ የሚያስደስታቸው ሁሉ ደስ ይበላቸው፤
“እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
ለአገልጋዩ ሁኔታዎች ሁሉ ሲሳኩለት እግዚአብሔር ደስ ይለዋል!” ይበሉ።
28አንደበቴ ቀኑን ሙሉ
ስለ ጽድቅህና ስለ ምስጋናህ ይናገራል።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997