መጽሐፈ መዝሙር 39
39
ሰው መከራ ሲደርስበት የሚያቀርበው ኑዛዜ
1እኔ “ድርጊቴንና አንደበቴን ከኃጢአት እጠብቃለሁ፤
በአጠገቤ ክፉ ሰው በሚገኝበት ጊዜ ሁሉ
አፌን እሸብባለሁ” ብዬ ቃል ገባሁ።
2አንድ ቃል እንኳ ሳልናገር ዝም አልኩ፤
መልካም ስለ ሆነ ነገር እንኳ አልተናገርኩም፤
ነገር ግን ሥቃዬ ከበፊት ይልቅ እየባሰ ሄደ።
3ልቤ በውስጤ ነደደ፤
በሐሳቤም እሳት ተያያዘ፤
ከዚያም መናገር ጀመርኩ።
4“ጌታ ሆይ!
መጨረሻዬንና የቀኖቼን ብዛት እንዳውቅ አድርገኝ፤
ዕድሜዬም ምን ያኽል አጭር እንደ ሆነ ንገረኝ።”
5የዘመኔን መለኪያ ከእጅ መዳፍ እንዳይበልጥ አድርገህ አሳጠርከው፤
ዕድሜዬም በአንተ ፊት ከምንም አይቈጠርም፤
በእርግጥ የሰው ሕይወት እንደ ነፋስ ሽውታ ነው።
6ሰው ከጥላም የተሻለ አይደለም፤
በከንቱ ይደክማል፤ ሀብትን ያከማቻል፤
ነገር ግን ማን እንደሚጠቀምበት አያውቅም።
7እግዚአብሔር ሆይ!
ታዲያ፥ እኔ ተስፋዬን በአንተ ላይ ከማድረግ በቀር
ሌላ ምን እጠብቃለሁ?
8ከኃጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤
ሞኞች እንዲሳለቁብኝ አታድርግ።
9ይህ ሁሉ እንዲደርስብኝ ያደረግኸው
አንተ ስለ ሆንክ ዝም እላለሁ፤
አንድ ቃል እንኳ አልናገርም።
10ከጽኑ አመታትህ የተነሣ በጣም ስለ ተዳከምኩ
መቅሠፍትህን ከእኔ አርቅ።
11ሰውን በኃጢአቱ ትገሥጸዋለህ፤ ትቀጣዋለህም፤
የሚወደውንም ነገር እንደ ብል ታጠፋበታለህ፤
በእርግጥ ሰው ከነፋስ ሽውታ የሚሻል አይደለም።
12እግዚአብሔር ሆይ!
ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤
ሳለቅስም ቶሎ ብለህ እርዳኝ፤
እኔ ለጥቂት ጊዜ የአንተ እንግዳ ነኝ፤
እንደ ቀድሞ አባቶቼም በስደተኛነት የምኖር ነኝ።
13ወደማልመለስበት ወደ ሞት ሳልሄድ
ጥቂት ደስታ እንዳገኝ እባክህ ታገሠኝ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 39: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 39
39
ሰው መከራ ሲደርስበት የሚያቀርበው ኑዛዜ
1እኔ “ድርጊቴንና አንደበቴን ከኃጢአት እጠብቃለሁ፤
በአጠገቤ ክፉ ሰው በሚገኝበት ጊዜ ሁሉ
አፌን እሸብባለሁ” ብዬ ቃል ገባሁ።
2አንድ ቃል እንኳ ሳልናገር ዝም አልኩ፤
መልካም ስለ ሆነ ነገር እንኳ አልተናገርኩም፤
ነገር ግን ሥቃዬ ከበፊት ይልቅ እየባሰ ሄደ።
3ልቤ በውስጤ ነደደ፤
በሐሳቤም እሳት ተያያዘ፤
ከዚያም መናገር ጀመርኩ።
4“ጌታ ሆይ!
መጨረሻዬንና የቀኖቼን ብዛት እንዳውቅ አድርገኝ፤
ዕድሜዬም ምን ያኽል አጭር እንደ ሆነ ንገረኝ።”
5የዘመኔን መለኪያ ከእጅ መዳፍ እንዳይበልጥ አድርገህ አሳጠርከው፤
ዕድሜዬም በአንተ ፊት ከምንም አይቈጠርም፤
በእርግጥ የሰው ሕይወት እንደ ነፋስ ሽውታ ነው።
6ሰው ከጥላም የተሻለ አይደለም፤
በከንቱ ይደክማል፤ ሀብትን ያከማቻል፤
ነገር ግን ማን እንደሚጠቀምበት አያውቅም።
7እግዚአብሔር ሆይ!
ታዲያ፥ እኔ ተስፋዬን በአንተ ላይ ከማድረግ በቀር
ሌላ ምን እጠብቃለሁ?
8ከኃጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤
ሞኞች እንዲሳለቁብኝ አታድርግ።
9ይህ ሁሉ እንዲደርስብኝ ያደረግኸው
አንተ ስለ ሆንክ ዝም እላለሁ፤
አንድ ቃል እንኳ አልናገርም።
10ከጽኑ አመታትህ የተነሣ በጣም ስለ ተዳከምኩ
መቅሠፍትህን ከእኔ አርቅ።
11ሰውን በኃጢአቱ ትገሥጸዋለህ፤ ትቀጣዋለህም፤
የሚወደውንም ነገር እንደ ብል ታጠፋበታለህ፤
በእርግጥ ሰው ከነፋስ ሽውታ የሚሻል አይደለም።
12እግዚአብሔር ሆይ!
ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴንም አድምጥ፤
ሳለቅስም ቶሎ ብለህ እርዳኝ፤
እኔ ለጥቂት ጊዜ የአንተ እንግዳ ነኝ፤
እንደ ቀድሞ አባቶቼም በስደተኛነት የምኖር ነኝ።
13ወደማልመለስበት ወደ ሞት ሳልሄድ
ጥቂት ደስታ እንዳገኝ እባክህ ታገሠኝ።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997