መጽሐፈ መዝሙር 40
40
የምስጋና መዝሙር
1እንዲረዳኝ በትዕግሥት ጌታን ተጠባበቅሁት።
ወደ እኔም መለስ ብሎ ጸሎቴን ሰማ።
2ከረግረግ ቦታና ጭቃማ ከሆነው
ከሚያዳልጥ ጒድጓድ አወጣኝ፤
እግሮቼን በአለት ድንጋይ ላይ አድርጎ
የምቆምበትን ጠንካራ ቦታ ሰጠኝ።
3በአንደበቴ አዲስ መዝሙር፥
እርሱም ለአምላካችን የምስጋና መዝሙር አኖረ፤
ብዙዎች በፍርሃት ተመልክተው
በእግዚአብሔርም ይታመናሉ።
4በእግዚአብሔር ብቻ የሚታመኑ፥
ወደ ጣዖቶች የማይመለሱ፥
ሐሰተኞች አማልክትን ከሚከተሉ
ከዐመፀኞች ሰዎች ጋር የማይተባበሩ የተባረኩ ናቸው።
5እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ!
ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርገህልናል፤
ከአንተ የሚወዳደር ማንም የለም፤
አንተ ለእኛ ያቀድክልንን መልካም ነገር
ማንም ሊቈጥረው አይችልም፤
እኔ ስለ እነርሱ በዝርዝር ለመናገርና ለማውራት ብሞክር
ቊጥራቸው እጅግ የበዛ ይሆንብኛል።
6አንተ መሥዋዕትንና መባን አትፈልግም፤
እንስሶች በመሠዊያ ላይ እንዲቃጠሉ፥
ወይም ለኃጢአት ስርየት የሚሆን መሥዋዕት እንዲቀርብልህ አትጠይቅም፤
በዚህ ፈንታ የአንተን ትእዛዝ በመስማት እንዳገለግልህ አደረግኸኝ። #ዕብ. 10፥5-7።
7ስለዚህ “ስለ እኔ በተጻፈው የሕግ መጽሐፍ መሠረት
እነሆ እኔ መጥቻለሁ።
8አምላኬ ሆይ! ፈቃድህን መፈጸም እወዳለሁ፤
ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው” አልኩ።
9በትልቁ ጉባኤ ፊት ትክክለኛውን ነገር ተናገርኩ፤
እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ እንደምታውቀው
ቃሌን ከመናገር አልቈጥበውም።
10ደግነትህን በልቤ ውስጥ አልደብቅም፤
ስለ ታማኝነትህና ስለ አዳኝነትህ ተናግሬአለሁ፤
ከትልቁ ጉባኤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንና እውነተኛነትህን አልሰውርም።
11እግዚአብሔር ሆይ! ምሕረትህን ከእኔ አታርቅ፤
ፍቅርህና ዘለዓለማዊ ታማኝነትህ ለዘለዓለም ይጠብቁኝ።
12ከቊጥር በላይ የሆኑ ችግሮች ያስጨንቁኛል!
በደሎቼ ስለ በዙ ማየት አልችልም፤
እነርሱም በቊጥር ከራስ ጠጒሮቼ ይበልጣሉ፤
ስለዚህ ልቤም እየከዳኝ ነው።
13እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አድነኝ፤
እግዚአብሔር ሆይ! ፈጥነህ እርዳኝ።
14ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ሁሉ
ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ።
የእኔን ጒዳት የሚመኙ ሁሉ
ኀፍረት ይድረስባቸው።
15በእኔ ውድቀት “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ
በኀፍረት ይሸማቀቁ።
16አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን
ደስ ይበላቸው፥ ሐሴትም ያድርጉ፤
ያንተን ማዳን የሚወዱ ዘወትር፦
“እግዚአብሔር ታላቅ ነው!” ይበሉ።
17አምላክ ሆይ! እኔ ችግረኛ ድኻ ነኝ፤
አንተ ግን አልረሳኸኝም፤
አንተ ረዳቴና አዳኜ ስለ ሆንክ
አሁንም በፍጥነት እርዳኝ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 40: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 40
40
የምስጋና መዝሙር
1እንዲረዳኝ በትዕግሥት ጌታን ተጠባበቅሁት።
ወደ እኔም መለስ ብሎ ጸሎቴን ሰማ።
2ከረግረግ ቦታና ጭቃማ ከሆነው
ከሚያዳልጥ ጒድጓድ አወጣኝ፤
እግሮቼን በአለት ድንጋይ ላይ አድርጎ
የምቆምበትን ጠንካራ ቦታ ሰጠኝ።
3በአንደበቴ አዲስ መዝሙር፥
እርሱም ለአምላካችን የምስጋና መዝሙር አኖረ፤
ብዙዎች በፍርሃት ተመልክተው
በእግዚአብሔርም ይታመናሉ።
4በእግዚአብሔር ብቻ የሚታመኑ፥
ወደ ጣዖቶች የማይመለሱ፥
ሐሰተኞች አማልክትን ከሚከተሉ
ከዐመፀኞች ሰዎች ጋር የማይተባበሩ የተባረኩ ናቸው።
5እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ!
ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርገህልናል፤
ከአንተ የሚወዳደር ማንም የለም፤
አንተ ለእኛ ያቀድክልንን መልካም ነገር
ማንም ሊቈጥረው አይችልም፤
እኔ ስለ እነርሱ በዝርዝር ለመናገርና ለማውራት ብሞክር
ቊጥራቸው እጅግ የበዛ ይሆንብኛል።
6አንተ መሥዋዕትንና መባን አትፈልግም፤
እንስሶች በመሠዊያ ላይ እንዲቃጠሉ፥
ወይም ለኃጢአት ስርየት የሚሆን መሥዋዕት እንዲቀርብልህ አትጠይቅም፤
በዚህ ፈንታ የአንተን ትእዛዝ በመስማት እንዳገለግልህ አደረግኸኝ። #ዕብ. 10፥5-7።
7ስለዚህ “ስለ እኔ በተጻፈው የሕግ መጽሐፍ መሠረት
እነሆ እኔ መጥቻለሁ።
8አምላኬ ሆይ! ፈቃድህን መፈጸም እወዳለሁ፤
ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው” አልኩ።
9በትልቁ ጉባኤ ፊት ትክክለኛውን ነገር ተናገርኩ፤
እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ እንደምታውቀው
ቃሌን ከመናገር አልቈጥበውም።
10ደግነትህን በልቤ ውስጥ አልደብቅም፤
ስለ ታማኝነትህና ስለ አዳኝነትህ ተናግሬአለሁ፤
ከትልቁ ጉባኤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንና እውነተኛነትህን አልሰውርም።
11እግዚአብሔር ሆይ! ምሕረትህን ከእኔ አታርቅ፤
ፍቅርህና ዘለዓለማዊ ታማኝነትህ ለዘለዓለም ይጠብቁኝ።
12ከቊጥር በላይ የሆኑ ችግሮች ያስጨንቁኛል!
በደሎቼ ስለ በዙ ማየት አልችልም፤
እነርሱም በቊጥር ከራስ ጠጒሮቼ ይበልጣሉ፤
ስለዚህ ልቤም እየከዳኝ ነው።
13እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አድነኝ፤
እግዚአብሔር ሆይ! ፈጥነህ እርዳኝ።
14ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ሁሉ
ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ።
የእኔን ጒዳት የሚመኙ ሁሉ
ኀፍረት ይድረስባቸው።
15በእኔ ውድቀት “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ
በኀፍረት ይሸማቀቁ።
16አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን
ደስ ይበላቸው፥ ሐሴትም ያድርጉ፤
ያንተን ማዳን የሚወዱ ዘወትር፦
“እግዚአብሔር ታላቅ ነው!” ይበሉ።
17አምላክ ሆይ! እኔ ችግረኛ ድኻ ነኝ፤
አንተ ግን አልረሳኸኝም፤
አንተ ረዳቴና አዳኜ ስለ ሆንክ
አሁንም በፍጥነት እርዳኝ።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997