መጽሐፈ መዝሙር 47
47
እግዚአብሔር የዓለም ሁሉ ንጉሥ ነው
1ሕዝቦች ሁሉ፥ በደስታ አጨብጭቡ!
ከፍ ባለ ድምፅ በመዘመር፥
እግዚአብሔርን አመስግኑ!
2በምድር ሁሉ ላይ ታላቁ ገዢ
ልዑል እግዚአብሔር ምንኛ አስፈሪ ነው?
3እርሱ ሕዝቦች ጸጥ ብለው እንዲገዙልንና
መንግሥታትም በቊጥጥራችን ሥር እንዲሆኑ አደረገ።
4ርስት አድርገን የምንይዛትን ምድር መረጠልን፤
ይህችም ምድር ለሚወድደው ለእስራኤል ሕዝብ መመኪያ ናት።
5እግዚአብሔር በእልልታና
በመለከት ድምፅ ዐረገ።
6ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ!
ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ!
7አምላካችን የዓለም ሁሉ ንጉሥ ነው፤
ስለዚህ የምስጋና መዝሙር ዘምሩለት!
8እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦአል፤
መንግሥታትንም የሚያስተዳድር እርሱ ነው።
9የመንግሥታት መሪዎች ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር ይሰበሰባሉ፤
የምድር ገዢዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ናቸውና፤
እርሱ ከሁሉም በላይ ከፍ ያለ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 47: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 47
47
እግዚአብሔር የዓለም ሁሉ ንጉሥ ነው
1ሕዝቦች ሁሉ፥ በደስታ አጨብጭቡ!
ከፍ ባለ ድምፅ በመዘመር፥
እግዚአብሔርን አመስግኑ!
2በምድር ሁሉ ላይ ታላቁ ገዢ
ልዑል እግዚአብሔር ምንኛ አስፈሪ ነው?
3እርሱ ሕዝቦች ጸጥ ብለው እንዲገዙልንና
መንግሥታትም በቊጥጥራችን ሥር እንዲሆኑ አደረገ።
4ርስት አድርገን የምንይዛትን ምድር መረጠልን፤
ይህችም ምድር ለሚወድደው ለእስራኤል ሕዝብ መመኪያ ናት።
5እግዚአብሔር በእልልታና
በመለከት ድምፅ ዐረገ።
6ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ!
ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ!
7አምላካችን የዓለም ሁሉ ንጉሥ ነው፤
ስለዚህ የምስጋና መዝሙር ዘምሩለት!
8እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦአል፤
መንግሥታትንም የሚያስተዳድር እርሱ ነው።
9የመንግሥታት መሪዎች ከአብርሃም አምላክ ሕዝብ ጋር ይሰበሰባሉ፤
የምድር ገዢዎች ሁሉ የእግዚአብሔር ናቸውና፤
እርሱ ከሁሉም በላይ ከፍ ያለ ነው።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997