መጽሐፈ መዝሙር 48
48
የእግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ጽዮን
1እግዚአብሔር ታላቅ ስለ ሆነ
በአምላካችን ከተማ፤
በተቀደሰ ተራራው ላይ
ከፍ ያለ ምስጋና ሊቀርብለት ይገባዋል።
2በሰሜን በኩል የምትገኘው፥ በከፍታዋና በውበትዋ የምትደነቀው፥
የጽዮን ተራራ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች፤
እርስዋም በምድር ላሉ ሁሉ ደስታን ታጐናጽፋለች። #ማቴ. 5፥35።
3እግዚአብሔር በምሽግዋ ውስጥ ነው፤
እርሱም ከለላዋ መሆኑን አስመስክሮአል።
4ከተማይቱን ለማጥቃት
ነገሥታት ኀይላቸውን አሰባሰቡ።
5ነገር ግን ባዩአት ጊዜ ደነገጡ፤
ፈርተውም ሸሹ።
6እዚያም ሳሉ በፍርሃት ተርበደበዱ፤
ምጥ እንደ ያዛትም ሴት ተጨነቁ።
7በምሥራቅ ነፋስ እንደሚሰባበሩ
የተርሴስ መርከቦች ሆኑ።
8እግዚአብሔር ያደረገውን ሰምተናል፤
አሁንም ሁሉን ቻይ ጌታ
የራሱ በሆነችው ከተማ ያደረገውን
በዐይናችን አየን፤
እርሱ ከተማይቱን ለዘለዓለም
ጸንታ እንድትኖር ያደርጋታል።
9አምላክ ሆይ! በመቅደስህ ውስጥ
ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህ እናስባለን።
10አምላክ ሆይ! ምስጋናህ እስከ ዓለም ዳርቻ እንደ ደረሰ
ስምህም እንደዚሁ ገናና ነው።
11ፍርድህ ትክክለኛ ስለ ሆነ
በጽዮን የሚኖሩ ሕዝቦች ደስ ይላቸዋል፤
በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ሐሴት ያደርጋሉ።
12ተሰልፋችሁ ጽዮንን ዙሩአት፤
ማማዎችዋንም ቊጠሩ።
13ለሚመጣው ትውልድ ታስተላልፉ ዘንድ
ጠንካራ ቅጥሮችዋን አስተውሉ፤
ምሽጎችዋንም ተመልከቱ።
14የምትነግሩአቸውም “እግዚአብሔር እንዲህ ነው፤
አምላካችን ዘለዓለማዊ ነው፤
ወደፊትም ለዘለዓለም ይመራናል” ብላችሁ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 48: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 48
48
የእግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ጽዮን
1እግዚአብሔር ታላቅ ስለ ሆነ
በአምላካችን ከተማ፤
በተቀደሰ ተራራው ላይ
ከፍ ያለ ምስጋና ሊቀርብለት ይገባዋል።
2በሰሜን በኩል የምትገኘው፥ በከፍታዋና በውበትዋ የምትደነቀው፥
የጽዮን ተራራ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች፤
እርስዋም በምድር ላሉ ሁሉ ደስታን ታጐናጽፋለች። #ማቴ. 5፥35።
3እግዚአብሔር በምሽግዋ ውስጥ ነው፤
እርሱም ከለላዋ መሆኑን አስመስክሮአል።
4ከተማይቱን ለማጥቃት
ነገሥታት ኀይላቸውን አሰባሰቡ።
5ነገር ግን ባዩአት ጊዜ ደነገጡ፤
ፈርተውም ሸሹ።
6እዚያም ሳሉ በፍርሃት ተርበደበዱ፤
ምጥ እንደ ያዛትም ሴት ተጨነቁ።
7በምሥራቅ ነፋስ እንደሚሰባበሩ
የተርሴስ መርከቦች ሆኑ።
8እግዚአብሔር ያደረገውን ሰምተናል፤
አሁንም ሁሉን ቻይ ጌታ
የራሱ በሆነችው ከተማ ያደረገውን
በዐይናችን አየን፤
እርሱ ከተማይቱን ለዘለዓለም
ጸንታ እንድትኖር ያደርጋታል።
9አምላክ ሆይ! በመቅደስህ ውስጥ
ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህ እናስባለን።
10አምላክ ሆይ! ምስጋናህ እስከ ዓለም ዳርቻ እንደ ደረሰ
ስምህም እንደዚሁ ገናና ነው።
11ፍርድህ ትክክለኛ ስለ ሆነ
በጽዮን የሚኖሩ ሕዝቦች ደስ ይላቸዋል፤
በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ሐሴት ያደርጋሉ።
12ተሰልፋችሁ ጽዮንን ዙሩአት፤
ማማዎችዋንም ቊጠሩ።
13ለሚመጣው ትውልድ ታስተላልፉ ዘንድ
ጠንካራ ቅጥሮችዋን አስተውሉ፤
ምሽጎችዋንም ተመልከቱ።
14የምትነግሩአቸውም “እግዚአብሔር እንዲህ ነው፤
አምላካችን ዘለዓለማዊ ነው፤
ወደፊትም ለዘለዓለም ይመራናል” ብላችሁ ነው።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997