መጽሐፈ መዝሙር 49
49
በሀብት የመተማመን ሞኝነት
1ሕዝቦች ሁሉ ይህን ስሙ!
በዓለም የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ!
2ከፍተኞችና ዝቅተኞች፥
ሀብታሞችና ድኾች ስሙ፤
3አንደበቴ የጥበብ ቃላትን ይናገራል፤
የልቤ ሐሳብም ማስተዋልን ያስገኛል።
4ሐሳቤን ወደ ምሳሌዎች አዘነብላለሁ፤
የምሳሌዎችንም ትርጒም
በገና በመደርደር እገልጣለሁ።
5ክፉ ቀን ሲመጣና ክፉዎች አታላዮች ሲከቡኝ
ለምን እፈራለሁ?
6እንዲሁም በሀብታቸው ብዛት የሚተማመኑና
በብልጽግናቸው ብዛት የሚመኩ
ክፉ ሰዎች ቢከቡኝስ ለምን እፈራለሁ?
7ሰው ራሱን መቤዠትም ሆነ
ለሕይወቱ ቤዛ የሚሆነውን ዋጋ
ለእግዚአብሔር መክፈል አይችልም።
8ለሰው ሕይወት የሚከፈለው ዋጋ
እጅግ ብዙ ነው፤
የቱንም ያኽል ቢከፈል በቂ አይሆንም።
9እንዳይሞትና ወደ መቃብር እንዳይወርድ፥
ለዘለዓለም እንዲኖር ለማድረግ
የቱንም ያኽል ቢከፈል በቂ አይሆንም።
10ማንም እንደሚያውቀው
ጠቢባን እንኳ ከሞኞችና ከሰነፎች እኩል ይሞታሉ፤
ሁሉም ሀብታቸውን ትተው ይሄዳሉ።
11ብዙ መሬት በየስማቸው የነበራቸው ቢሆንም እንኳ
መቃብር የዘለዓለም ቤታቸውና መኖሪያቸው ነው።
12ሰው ምንም ሀብታም ቢሆን ዘለቄታ የለውም፤
እንደ እንስሶች ይሞታል።
13ይህ በራሳቸው የሚተማመኑ የሞኞችና
የእነርሱን አባባል የሚቀበሉ ሰዎች ዕድል ፈንታ ነው።
14እነዚህ እንደ በጎች እንዲሞቱና እንዲቀበሩ ይደረጋሉ፤
እረኛ በጎችን እንደሚመራ ሞትም እነዚህን ወደ መቃብር ይመራል፤
ትክክለኞች ሰዎች በማለዳ በመቃብራቸው ላይ ይመላለሳሉ፤
ሥጋቸውም በመቃብር ውስጥ ይበሰብሳል፤
የሙታን ዓለምም መኖሪያቸው ይሆናል።
ደጋግ ሰዎችም በማለዳ ተነሥተው
በእነርሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ።
15እግዚአብሔር ግን ሕይወቴን በመታደግ
ከሲኦል ኀይልም አውጥቶ ወደ እርሱ ይወስደኛል።
16ሰው ሀብታም ሲሆን፥
የቤቱም ብልጽግና እየበዛ ሲሄድ አትፍራው፤
17በሚሞትበት ጊዜ ምንም ነገር አይወስድም፤
ሀብቱም ከእርሱ ጋር ወደ መቃብር አይወርድም።
18ሰው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ቢደሰትና
ሁሉም ነገር ስለ ተሳካለት ቢመሰገንም እንኳ
19በሞት ተለይቶ ዳግመኛ ብርሃንን ወደማያይበት
ወደ ቀድሞ አባቶቹ ይሄዳል።
20ያለ ማስተዋል ሀብት ያካበተ ሰው
እንደ እንስሳ መሞቱ አይቀርም።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 49: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 49
49
በሀብት የመተማመን ሞኝነት
1ሕዝቦች ሁሉ ይህን ስሙ!
በዓለም የምትኖሩ ሁሉ ይህን አድምጡ!
2ከፍተኞችና ዝቅተኞች፥
ሀብታሞችና ድኾች ስሙ፤
3አንደበቴ የጥበብ ቃላትን ይናገራል፤
የልቤ ሐሳብም ማስተዋልን ያስገኛል።
4ሐሳቤን ወደ ምሳሌዎች አዘነብላለሁ፤
የምሳሌዎችንም ትርጒም
በገና በመደርደር እገልጣለሁ።
5ክፉ ቀን ሲመጣና ክፉዎች አታላዮች ሲከቡኝ
ለምን እፈራለሁ?
6እንዲሁም በሀብታቸው ብዛት የሚተማመኑና
በብልጽግናቸው ብዛት የሚመኩ
ክፉ ሰዎች ቢከቡኝስ ለምን እፈራለሁ?
7ሰው ራሱን መቤዠትም ሆነ
ለሕይወቱ ቤዛ የሚሆነውን ዋጋ
ለእግዚአብሔር መክፈል አይችልም።
8ለሰው ሕይወት የሚከፈለው ዋጋ
እጅግ ብዙ ነው፤
የቱንም ያኽል ቢከፈል በቂ አይሆንም።
9እንዳይሞትና ወደ መቃብር እንዳይወርድ፥
ለዘለዓለም እንዲኖር ለማድረግ
የቱንም ያኽል ቢከፈል በቂ አይሆንም።
10ማንም እንደሚያውቀው
ጠቢባን እንኳ ከሞኞችና ከሰነፎች እኩል ይሞታሉ፤
ሁሉም ሀብታቸውን ትተው ይሄዳሉ።
11ብዙ መሬት በየስማቸው የነበራቸው ቢሆንም እንኳ
መቃብር የዘለዓለም ቤታቸውና መኖሪያቸው ነው።
12ሰው ምንም ሀብታም ቢሆን ዘለቄታ የለውም፤
እንደ እንስሶች ይሞታል።
13ይህ በራሳቸው የሚተማመኑ የሞኞችና
የእነርሱን አባባል የሚቀበሉ ሰዎች ዕድል ፈንታ ነው።
14እነዚህ እንደ በጎች እንዲሞቱና እንዲቀበሩ ይደረጋሉ፤
እረኛ በጎችን እንደሚመራ ሞትም እነዚህን ወደ መቃብር ይመራል፤
ትክክለኞች ሰዎች በማለዳ በመቃብራቸው ላይ ይመላለሳሉ፤
ሥጋቸውም በመቃብር ውስጥ ይበሰብሳል፤
የሙታን ዓለምም መኖሪያቸው ይሆናል።
ደጋግ ሰዎችም በማለዳ ተነሥተው
በእነርሱ ላይ ሥልጣናቸውን ያሳያሉ።
15እግዚአብሔር ግን ሕይወቴን በመታደግ
ከሲኦል ኀይልም አውጥቶ ወደ እርሱ ይወስደኛል።
16ሰው ሀብታም ሲሆን፥
የቤቱም ብልጽግና እየበዛ ሲሄድ አትፍራው፤
17በሚሞትበት ጊዜ ምንም ነገር አይወስድም፤
ሀብቱም ከእርሱ ጋር ወደ መቃብር አይወርድም።
18ሰው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ቢደሰትና
ሁሉም ነገር ስለ ተሳካለት ቢመሰገንም እንኳ
19በሞት ተለይቶ ዳግመኛ ብርሃንን ወደማያይበት
ወደ ቀድሞ አባቶቹ ይሄዳል።
20ያለ ማስተዋል ሀብት ያካበተ ሰው
እንደ እንስሳ መሞቱ አይቀርም።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997