መጽሐፈ መዝሙር 50
50
እውነተኛ አምልኮ
1ኀያሉ እግዚአብሔር አምላክ ይናገራል፤
ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ፥
በምድር ያለውን ሰው ሁሉ ይጠራል።
2እግዚአብሔር በውበትዋ ፍጹም ከሆነችው
ከጽዮን ከተማ የደመቀ ብርሃንን ያበራል።
3አምላካችን ይመጣል፤ ዝም አይልም፤
የሚያቃጥል እሳት በፊቱ ነው፤
ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው ነው።
4በሕዝቡ ላይ ሲፈርድ
ሰማይንና ምድርን ለምስክርነት ይጠራል።
5“በመሥዋዕት ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን የገቡትን
ታማኞች አገልጋዮቼን ሰብስቡልኝ” ይላል።
6እግዚአብሔር ብቸኛ ዳኛ ስለ ሆነ
ሰማያት የእርሱን ፍትሕ ያውጃሉ።
7ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦
“ሕዝቤ ሆይ! ቃሌን ስማ፤
እስራኤል ሆይ! በአንተ ላይ እመሰክራለሁ፤
እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።
8ስለ መሥዋዕትህና ዘወትር ስለምታቀርበው
የሚቃጠል መባ አልወቅስህም።
9እንዲሁም ከበረትህ ኰርማዎችን፥
ከጒሮኖህም አውራ ፍየሎችን ልወስድብህ አልፈልግም።
10በዱር ያሉ አራዊትና
በሺህ የሚቈጠሩ ተራራዎች ላይ የሚሰማሩት
የእንስሶች መንጋዎች የእኔ ናቸው።
11የተራራ ወፎችን ሁሉ ዐውቃቸዋለሁ
በመስክ የሚገኙ እንስሶች ሁሉ የእኔ ናቸው።
12“ዓለምና በውስጥዋ ያለው ነገር ሁሉ የእኔ ስለ ሆነ
የምራብ ብሆን እንኳ ለአንተ አልነግርህም ነበር።
13የኰርማዎችን ሥጋ እበላለሁን?
ወይስ የፍየሎችን ደም እጠጣለሁን?
14የምስጋና መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርብ፤
ስእለትህንም ለልዑል ስጥ።
15መከራ በሚደርስብህ ጊዜ ጥራኝ፤
እኔም አድንሃለሁ፤
አንተም ታከብረኛለህ።”
16ኃጢአተኛውን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፤
“ሕጌን ለማንበብ፥
ቃል ኪዳኔን በአንደበትህ ለመግለጽ ምን መብት አለህ?
17ስሕተትህን መታረም ትጠላለህ፤
ቃሎቼንም ትንቃለህ።
18ሌባውን ስታይ ከእርሱ ጋር ትወዳጃለህ፤
ከአመንዝራዎችም ጋር በመስማማት ትተባበራለህ።
19“ክፉ ነገር ለመናገር ለአንደበትህ ነጻነትን ሰጠኸው፤
ንግግርህም ሁሉ ሽንገላ ብቻ ነው።
20በወንድምህ ላይ ሁልጊዜ ክፉ ነገር ትናገራለህ፤
የእናትህንም ልጅ ታማለህ።
21ይህን ስታደርግ ዝም በማለቴ
እኔም እንደ አንተ የሆንኩ መሰለህን?
አሁን ግን ፊት ለፊት ነገሩን ገልጬ እገሥጽሃለሁ።
22“ስለዚህ እናንተ እኔን የምትንቁ ሁሉ ይህን አስተውሉ፤
አለበለዚያ አጠፋችኋለሁ፤
የሚያድናችሁም የለም።
23የምስጋና መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤
መንገዴን ለሚከተል አዳኝነቴን አሳየዋለሁ።”
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 50: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 50
50
እውነተኛ አምልኮ
1ኀያሉ እግዚአብሔር አምላክ ይናገራል፤
ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያዋ ድረስ፥
በምድር ያለውን ሰው ሁሉ ይጠራል።
2እግዚአብሔር በውበትዋ ፍጹም ከሆነችው
ከጽዮን ከተማ የደመቀ ብርሃንን ያበራል።
3አምላካችን ይመጣል፤ ዝም አይልም፤
የሚያቃጥል እሳት በፊቱ ነው፤
ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው ነው።
4በሕዝቡ ላይ ሲፈርድ
ሰማይንና ምድርን ለምስክርነት ይጠራል።
5“በመሥዋዕት ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን የገቡትን
ታማኞች አገልጋዮቼን ሰብስቡልኝ” ይላል።
6እግዚአብሔር ብቸኛ ዳኛ ስለ ሆነ
ሰማያት የእርሱን ፍትሕ ያውጃሉ።
7ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦
“ሕዝቤ ሆይ! ቃሌን ስማ፤
እስራኤል ሆይ! በአንተ ላይ እመሰክራለሁ፤
እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።
8ስለ መሥዋዕትህና ዘወትር ስለምታቀርበው
የሚቃጠል መባ አልወቅስህም።
9እንዲሁም ከበረትህ ኰርማዎችን፥
ከጒሮኖህም አውራ ፍየሎችን ልወስድብህ አልፈልግም።
10በዱር ያሉ አራዊትና
በሺህ የሚቈጠሩ ተራራዎች ላይ የሚሰማሩት
የእንስሶች መንጋዎች የእኔ ናቸው።
11የተራራ ወፎችን ሁሉ ዐውቃቸዋለሁ
በመስክ የሚገኙ እንስሶች ሁሉ የእኔ ናቸው።
12“ዓለምና በውስጥዋ ያለው ነገር ሁሉ የእኔ ስለ ሆነ
የምራብ ብሆን እንኳ ለአንተ አልነግርህም ነበር።
13የኰርማዎችን ሥጋ እበላለሁን?
ወይስ የፍየሎችን ደም እጠጣለሁን?
14የምስጋና መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርብ፤
ስእለትህንም ለልዑል ስጥ።
15መከራ በሚደርስብህ ጊዜ ጥራኝ፤
እኔም አድንሃለሁ፤
አንተም ታከብረኛለህ።”
16ኃጢአተኛውን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፤
“ሕጌን ለማንበብ፥
ቃል ኪዳኔን በአንደበትህ ለመግለጽ ምን መብት አለህ?
17ስሕተትህን መታረም ትጠላለህ፤
ቃሎቼንም ትንቃለህ።
18ሌባውን ስታይ ከእርሱ ጋር ትወዳጃለህ፤
ከአመንዝራዎችም ጋር በመስማማት ትተባበራለህ።
19“ክፉ ነገር ለመናገር ለአንደበትህ ነጻነትን ሰጠኸው፤
ንግግርህም ሁሉ ሽንገላ ብቻ ነው።
20በወንድምህ ላይ ሁልጊዜ ክፉ ነገር ትናገራለህ፤
የእናትህንም ልጅ ታማለህ።
21ይህን ስታደርግ ዝም በማለቴ
እኔም እንደ አንተ የሆንኩ መሰለህን?
አሁን ግን ፊት ለፊት ነገሩን ገልጬ እገሥጽሃለሁ።
22“ስለዚህ እናንተ እኔን የምትንቁ ሁሉ ይህን አስተውሉ፤
አለበለዚያ አጠፋችኋለሁ፤
የሚያድናችሁም የለም።
23የምስጋና መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤
መንገዴን ለሚከተል አዳኝነቴን አሳየዋለሁ።”
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997