ወደ ሮም ሰዎች 14
14
በሰው ላይ አለመፍረድ
1በእናንተ መካከል በእምነቱ ደካማ የሆነውን ሰው ተቀበሉት እንጂ በግል ሐሳቡ ላይ ክርክር አታንሡ። 2ለምሳሌ አንድ ሰው ማንኛውንም ነገር ለመብላት የሚያስችል እምነት ይኖረዋል፤ በእምነቱ ያልጸናው ሰው ግን አትክልት ብቻ ይበላል፤ 3ስለዚህ ማንኛውንም ነገር የሚበላ ሰው የማይበላውን ሰው አይንቀፈው፤ የማይበላውም በሚበላው ሰው ላይ አይፍረድ፤ እርሱንም እግዚአብሔር ተቀብሎታልና። 4ታዲያ፥ በሌላ ሰው አገልጋይ ላይ የምትፈርድ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ የጌታው ጉዳይ ነው። እንዲያውም እግዚአብሔር ሊያቆመው ስለሚችል ጸንቶ ይቆማል።
5እንዲሁም አንዱ ቀን ከሌላው ቀን ይበልጥ ክቡር ነው ብሎ የሚያስብ ይኖር ይሆናል፤ ሌላው ደግሞ ቀኖች ሁሉ እኩል ክብር አላቸው እንጂ በቀኖች መካከል ልዩነት የለም ብሎ ያስባል። እንግዲህ ይህን በመሳሰለው ነገር እያንዳንዱ ሰው ከልቡ ያመነበትን ያድርግ። 6አንዱን ቀን ከሌላው ቀን አስበልጦ የሚያከብር ቢኖር ይህን ማድረጉ ለጌታ ክብር ብሎ ነው፤ ማንኛውንም ምግብ የሚበላ ለጌታ ክብር ብሎ ይበላል፤ ስለሚበላውም ምግብ እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤ ማንኛውንም ምግብ የማይበላ ለጌታ ክብር ብሎ አይበላም፤ ባለመብላቱም እግዚአብሔርን ያመሰግናል። #ቆላ. 2፥16። 7ከእኛ እያንዳንዱ ሕይወቱም ሆነ ሞቱ የራሱ አይደለም። 8ብንኖር ለጌታ እንኖራለን፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን፤ ስለዚህ ብንኖርም፥ ብንሞትም የጌታ ነን። 9ስለዚህ ክርስቶስ ሞቶ ከሞት የተነሣው የሕያዋንና የሙታን ጌታ ለመሆን ነው። 10ታዲያ፥ አንተ በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ? ወይስ ወንድምህን ለምን ትንቀዋለህ? ሁላችንም በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለን። #2ቆሮ. 5፥10። 11ምክንያቱም፦
“እኔ ሕያው ነኝ ይላል እግዚአብሔር፤
ሰው ሁሉ በጒልበቱ በእኔ ፊት ይንበረከካል፤
በአንደበቱም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ይመሰክራል” ተብሎ ተጽፎአል። #ኢሳ. 45፥23።
12ስለዚህ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ሥራ በእግዚአብሔር ፊት ቀርበን መልስ እንሰጣለን።
ለሰው እንቅፋት ከመሆን መጠንቀቅ
13ስለዚህ አንዳችን በአንዳችን ላይ አንፍረድ፤ ነገር ግን ማንም ሰው በወንድሙ መንገድ መሰናክል ወይም እንቅፋት ላለማኖር ይጠንቀቅ። 14አንድን ነገር ርኩስ ነው ብሎ ለሚያስብ ሰው ያ ነገር ለእርሱ ርኩስ ይሆንበታል እንጂ ማንኛውም ነገር በራሱ ርኩስ እንዳልሆነ እኔ በጌታ ኢየሱስ ዐውቄ አረጋግጣለሁ። 15አንተ በምትበላው ምግብ ምክንያት ለወንድምህ እንቅፋት ከሆንክ በፍቅር የምትኖር አይደለህም፤ ስለዚህ ክርስቶስ የሞተለትን ሰው በምትበላው ምግብ ምክንያት እንዲጠፋ አታድርግ። 16እንግዲህ በእናንተ ዘንድ መልካም የሆነውን ነገር ሌሎች እንዲነቅፉት አታድርጉ። 17የእግዚአብሔር መንግሥት በመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ጽድቅ፥ ሰላምና ደስታ ነው እንጂ የመብልና የመጠጥ ጉዳይ አይደለም። 18በዚህ ሁኔታ ክርስቶስን የሚያገለግል ሰው እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል፤ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው።
19ስለዚህ ሰላም የሚገኝበትንና እርስ በርሳችን የምንታነጽበትን ነገር እንከተል። 20በምግብም ምክንያት የእግዚአብሔርን ሥራ አናፍርስ። ምግብ ሁሉ ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ሌላውን ሰው የሚያሰናክል ምግብ መብላት ስሕተት ነው። 21ስለዚህ ወንድምህን ላለማሰናከል ሥጋን አለመብላት፥ የወይን ጠጅን አለመጠጣት፥ ወይም ማንኛውንም የሚያሰናክል ነገር አለማድረግ መልካም ነው። 22እንግዲህ ይህ እምነትህ በአንተና በእግዚአብሔር መካከል ይሁን፤ ትክክል ነው ብሎ የሚያምንበትን ነገር ሲያደርግ ኅሊናው የማይወቅሰው ሰው የተመሰገነ ነው። 23እየተጠራጠረ የሚበላ ሰው ግን ድርጊቱ በእምነት ላይ የተመሠረተ ስላልሆነ ይፈረድበታል፤ በእምነት ያልተደረገ ነገር ሁሉ ኃጢአት ነው።
Currently Selected:
ወደ ሮም ሰዎች 14: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: