1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3
3
ስለ ባልና ሚስት
1 #
ኤፌ. 5፥22፤ ቈላ. 3፥18። እንዲሁም እናንተ ሚስቶች ሆይ! ለባሎቻችሁ ታዘዙ፤ በዚህ ዓይነት አንዳንዶች በቃሉ የማያምኑ ቢሆኑም እንኳ ያለ ቃል በሚስቶቻቸው ጠባይ ብቻ ሊሳቡ ይችሉ ይሆናል። 2የሚሳቡትም አክብሮት የተሞላውንና ንጹሕ ኑሮአችሁን ሲመለከቱ ነው። 3#1ጢሞ. 2፥9።ለእናንተም ቢሆን ውበታችሁ ውጫዊ የሆነ፥ ሹሩባ በመሠራት፥ በወርቅ በማጌጥና የከበረ ልብስ በመልበስ አይሁን፤ 4ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጽሞና መንፈስ የተዋበው የተሰወረ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን። 5በዚህ ዓይነት ተስፋቸውን በእግዚአብሔር ላይ የጣሉ የቀድሞ ቅዱሳት ሴቶች ለባሎቻቸው በመገዛት ራሳቸውን ያስውቡ ነበር። 6#ዘፍ. 18፥12።ሣራም አብርሃምን “ጌታዬ” እያለች ትታዘዘው ነበር፤ እናንተም ምንም ሳያስፈራችሁ መልካም ብታደርጉ የእርሷ ልጆች ናችሁ።
7 #
ኤፌ. 5፥25፤ ቈላ. 3፥19። እናንተም ባሎች ሆይ! ጸሎታችሁ እንዳይደናቀፍ ከሚስቶቻችሁ ጋር በመተሳሰብ ኑሩ፤ የሕይወትንም ጸጋ አብረዋችሁ ስለሚወርሱ እንደ ደካማነታቸው ሴቶችን አክብሯቸው።
መልካም በማድረግ መከራን መቀበል
8በመጨረሻም ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፤ እርስ በእርሳችሁ ተሳሰቡ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ። 9ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም በረከትን ልትወርሱ ተጠርታችኋል።
10 #
መዝ. 34፥12-16። “ሕይወትን የሚወድ
መልካም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ፥
ምላሱን ከክፉ ይጠብቅ
ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤
11ከክፉም ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ፤
ሰላምን ይሻት፤ ይከተላትም።
12የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤
ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው የተከፈቱ ናቸው፤
የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።”
13ለመልካም ነገር ቀናኢ ብትሆኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው? 14#ማቴ. 5፥10።#ኢሳ. 8፥12፤13።ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራን ብትቀበሉ ብፁዓን ናችሁ። ዛቻቸውንም አትፍሩ፤ አትታወኩም። 15ነገር ግን ክርስቶስን ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተም ስላለች ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ 16ነገር ግን በገርነትና በአክብሮት አድርጉት፤ በክርስቶስ ያላችሁን መልካም ጠባይ በመንቀፍ የሚናገሩ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ መልካም ሕሊና ይኑራችሁ። 17የእግዚእብሔር ፈቃድ ከሆነ፥ ክፉ ሠርቶ መከራ ከመቀበል ይልቅ መልካም አድርጎ መከራ መቀበል ይሻላል። 18ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ። 19በዚያው መንፈስ በእስር ቤት ወዳሉት ነፍሳት ሄዶ ሰበከላቸው፤ 20#ዘፍ. 6፥1—7፥24።እነዚህ ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲሠራ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በውሃ የዳኑት ጥቂት ሲሆኑ እነርሱም ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ። 21ይህ ውሃ አሁን የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ እናንተን ያድናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ ሳይሆን፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የበጎ ሕሊና ልመና ነው። 22እርሱም ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ፤ መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ተገዝተውለታል።
Currently Selected:
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: