1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል መግቢያ
መግቢያ
መጽሐፉ ስያሜውን ያገኘው በእሥራኤል ታሪክ የመጀመሪያዎቹ የሆኑትን ነገሥታት ሳኦልንና ዳዊትን በቀባው (1ሳሙ. 10፥1፤ 16፥13) እንዲሁም በመሳፍንትና በነገሥታት መካከል እሥራኤልን በመስፍንነት፥ በነቢይነት፥ በካህንነት በማገልገል ታላቅ መንፈሳዊ ሥራን በሠራው (1ሳሙ. 3፥20) በነቢዩ ሳሙኤል ስም ነው።
የዕብራይስጡ መጽሐፍ ቅዱስ አንደኛና ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤልን እንደ አንድ መጽሐፍ ይቆጥረዋል። መጽሐፉ ለሁለት የተከፈለው የግብጽ ንጉሥ ፍላደልፈስ በ 285-247 ከክርስቶስ ልደት በፊት በገዛበት ዘመን፥ ብሉይ ኪዳንን ከዕብራይስጥ ወደ ግሪክ ሲተረጎም ነው። የሰባ ሊቃናት ትርጒም መጽሐፈ ሳሙኤልን የእሥራኤል የነገሥታት ዘመን ጅማሬን የሚያወሳ መጽሐፍ በመሆኑ “አንደኛና ሁለተኛ ነገሥት” በማለት ሰይሞታል። ሌሎች ሊቃውንት ግን መጽሐፉን ሲተረጕሙ ከዕብራይስጡ ስያሜውን በመውሰድ “መጽሐፈ ሳሙኤል” ይላሉ፤ አከፋፈሉን ደግሞ ከግሪኩ ወስደው “አንደኛና ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል” በማለት ሰይመውታል።
የመጽሐፉ አወቃቀር፦ አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል ከሦስት ዋና ዋና ክፍሎች የተዋቀረ ነው። የመጀመሪያው ክፍል ከምዕራፍ አንድ እስከ ምዕራፍ ስምንት ያለው ሲሆን፥ በዚህ ክፍል ስለ ሳሙኤል ልደት፥ እንደ ካህን፥ ነቢይና መስፍን ሆኖ እሥራኤልን ስለ ማስተዳደሩ፥ እንዲሁም የቃል ኪዳኑ ታቦት በፍልስጢኤማውያን ስለ መማረኩና ተአምራት ስለ መሥራቱን ያትታል። ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ከምዕራፍ ዘጠኝ እስከ ዐሥራ አምስት ያለው ነው። ይህም ሳኦል የመጀመሪያው የእሥራኤል ንጉሥ ሆኖ መመረጡን፥ ፍልስጢኤማውያን በጦርነት ድል ማድረጉንና እግዚአብሔር ያዘዘውን ባለመፈጸሙ የደረስበትን ውድቀት ያሳያል። ሦስተኛውና የመጨረሻው ክፍል ከምዕራፍ ዐሥራ ስድስት እስከ ሠላሳ አንድ ያለው ሲሆን፥ ዳዊት ለንጉሥነት መቀባቱ፥ ጎልያድን ማሸነፉን፥ እንዲሁም በሳኦል መሰደዱንና ሌሎች ተያያዥ ታሪኮችን የያዘ ነው።
መጸሐፈ ሳሙኤል የዘመነ መሳፍንትና የዘመነ ነገሥት መሸጋገሪያ እንደመሆኑ መጠን ምዕራፍ ሰባት የሚጀምረው በዘመነ መሳፍንት ማብቂያ ላይ ነው። ይህም እሥራኤልን ስለ መራውና የመጀመሪያዎቹን የእሥራኤል ነገሥታት ሳኦልንና ዳዊትን ስለቀባው ስለ ነቢዩ ሳሙኤል ቤተሰብ ሁኔታና መወለድ በማተት ነው። በተጨማሪም ስለ ዔሊ ቸልተኝነት፥ ስለ ቃል ኪዳኑ ታቦት መማረክ፥ ታቦቱ በተማረከበት ጊዜ ስለ ዔሊ መደንገጥ፥ ሁለቱ ልጆቹ ደግሞ በጦርነት ስለ መሞታቸው ይተርካል። የቃል ኪዳኑ ታቦት በፍልስጥኤማውያን መካከል በቆየባቸው ጊዜያት የፍልስጠኤማውያን አምላክ ዳጎን ከመሰባበሩም በላይ በሕዝቡ ላይ መቅሰፍት በመውረዱ ፍልስጥኤማውያን ተማክረው የቃል ኪዳኑን ታቦት ለመመለስ ወሰኑ። ከዚህ በኋላም በአንደኛ ሳሙኤል ላይ የምናነበው እሥራኤላውያን ንጉሥ እንዲነግሥላቸውና እንዲያስተዳድራቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ነው፤ በጥያቄአቸውም መሠረት ሳኦል የመጀመሪያ ንጉሥ ሆኖ ተሾመ። ሳኦል በመውደቁም በእርሱ ፈንታ ዳዊት ነገሠ።
ከዚህ መጽሐፍ ዐበይት መልእክቶች አንዱ እግዚአብሔር ለአምልኮቱና ለትእዛዛቱ ግድ የለሽ በሚሆኑት፥ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ይልቅ ለራሳቸው ፈቃድ ቅድሚያ በሚሰጡት ሰዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቅጣት እንደሚያመጣ ሲሆን፥ ለታማኞች ግን በረከት እንደሚሰጥ ነው። ለዚህም መረጃ የሚሆነን የአፍኒንና የፊንሐስ በጦርነት መገደል ነው፤ እንዲሁም የሊቀ ካህኑ የዔሊ መሞት፥ የሳኦል ከክብሩ መዋረድ፥ በአንጻሩም የሳሙኤል መመረጥና የዳዊት መቀባት ይገኙበታል። ሌላው ዐቢይ መልእክት እግዚአብሔር ታናናሾችንም የሚያከብርና ከፍ ከፍ የሚያደርግ አምላክ መሆኑን የሚያመለክት ነው። ለዚህም ማስረጃ የሚሆነው የይሁዳ ነገድ እያለ ከእስራኤል ነገዶች ታናሽ ከሆነው ከቢንያም ነገድ የወጣው ሳኦል የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ ሆኖ መመረጡ ነው፤ በሌላ በኩል ሊቀ ካህኑ ዔሊ እያለ ለብላቴናው ለሳሙኤል ተገልጦ መልዕክቱን ማስተላለፉ ሊስተዋል የሚገባ ጉዳይ ነው። እንዲሁም በእሴይ ቤት መልከ መልካሞቹ ኤልያብና ወንድሞቹ እያሉ ብላቴንውንና እረኛውን ዳዊት ለንጉሥነት መምረጡ የዚህ ማስረጃ ነው። ሌላው ዐብይ መልእክት በእስራኤል አገር መንግሥት እንዴት እንደ ተመሠረተ መግለጹ ነው።
የመጽሐፉ አጠቃላይ ይዘት
ሀ. ከዔሊ እስከ መሳፍንት ዘመን ያለው የእስራኤል ታሪክ (1፥1—8፥22)
የሳሙኤል መወለድ፥ የዔሊ ልጆች ኃጢአት (1፥1—2፥36)
የእግዚአብሔር ለሳሙኤል መገለጥና የቃል ኪዳኑ ታቦት መማረክ (3፥1—6፥21)
የሳሙኤል የመስፍንነት ዘመንና እስራኤል ንጉሥ ለማንገሥ ያቀረቡት ጥያቄ (7፥1—8፥22)
ለ. የሳኦል ዘመነ መንግሥት (9፥1—15፥35)
የሳኦል መቀባትና መንገሥ (9፥1—10፥27)
ሳኦል በጦርነት ያገኝዐው ድልና የሳሙኤል የመሰናበቻ ንግግር (11፥1—12፥25)
በሳኦል ዘመን ከፍልስጢኤማውያን ጋር የተደረገ ጦርነት (13፥1—14፥52)
የሳኦል ውድቀት (15)
ሐ. የንጉሥነት ሥልጣን ከሳኦል ወደ ዳዊት መሸጋገሩ (16፥1—31፥13)
ዳዊት ለንጉሥነት መቀባቱና ጎልያድን ድል በማድረግ ያገኘው ክብር (16፥1—18፥30)
ሳኦል ዳዊትን ማሳደዱ (19፥1—28፥25)
የፍልስጢኤማውያን ዳዊትን መቃወምና በአማሌቃዉይን ላይ የተደረገ ጦርነት (29፥1—31፥13)
ምዕራፍ
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል መግቢያ: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: