መጽሐፈ ሩት 4
4
የቦዔዝና የሩት ጋብቻ
1ቦዔዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ከዚህ በፊት ቦዔዝ ስለ እርሱ የተናገረው የእርሱ የቅርብ ዘመድ ወደዚያው ቦታ መጣ፤ ቦዔዝም ጠርቶ፦ “ወዳጄ ሆይ! ቀረብ በልና አጠገቤ ተቀመጥ” አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።#ሩት 3፥12። 2ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች ዐሥር ሰዎች ጠርቶ፦ “በዚህ ተቀመጡ” አላቸው። እነርሱም ተቀመጡ። 3ቦዔዝም የቅርብ ዘመዱን፦ “ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ናዖሚ የወንድማችንን ኤሊሜሌክን መሬት መሸጥ ትፈልጋልች። 4አንተም ስለዚህ ጉዳይ ማወቅ የሚገባህ ይመስለኛል፤ እንግዲህ መሬቱን ከፈለግኸው እዚህ በተቀመጡትና በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት ለራስህ ልታስቀረው ትችላለህ፤ የማትፈልገው ከሆነ ግን ቁርጡን ንገረኝ፤ መሬቱን የማስቀረት ቅድሚያ ያለህ አንተ ነህ፤ ከአንተም ቀጥሎ እኔ ነኝ።” ሰውየውም “እኔም እቤዥዋለሁ” አለ።#ዘሌ. 25፥25። 5ቦዔዝም “መሬቱን ከናዖሚ የምትገዛ ከሆነ በውርሱ የሟቹን ስም ታስጠራ ዘንድ ባልዋ የሞተባትን ሞአባዊትዋን ሩትንም አብረህ ትወስዳለህ” አለው።#ሩት 3፥13። 6የቅርብ ዘመዱም፦ “የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መውሰድ አልችልም፥ እኔ የራሴ ላደርገው አልችልምና አንተ እንድትወስደው ፈቅጄልሃለሁ” አለው።#4፥6 መሬቱን ለመግዛት ዘመድ የሆነው ሰው ተስማምቷል፤ ቦዔዝም ከሩት ጋር በመጋባቱ የቤተዘመድ ጋብቻ አያያዘ። ከእንደዚህ ጋብቻ የተወለደ ልጅ የማሕሎን እና የኤልሜሌክ ሕጋዊ ወራሽ ይሆናል። እናም ለግዢ የቀረበው መሬትም ለእሱ ይመለስለታል። ቅርብ የሆነው የመጀመርያው ዘመድ ገንዘብ ማውጣት ባለመፈለጉ መብቱን አሳልፎ ሰጠ።
7በጥንት ጊዜም፥ ማንም ቢሸጥ ቢለውጥም፥ ነገሩን ለማጽናት ሰው ጫማውን እንዲያወልቅ ለባልንጀራውም እንዲሰጠው በእስራኤል ዘንድ ልማድ ነበረ። ይህም በእስራኤላውያን ዘንድ ውል ለመፈጸሙ ማረጋገጫ ነበር። 8የቅርብ ዘመዱም ቦዔዝን፦ “አንተ ግዛው” አለው፤ ጫማውንም አወለቀ። 9ቦዔዝም ሽማግሌዎችንና ሕዝቡን ሁሉ፦ “ለኤሊሜሌክና ለኬሌዎን ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከናዖሚን እጅ እንደ ገዛሁ እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ። 10ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፥ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ” አላቸው። 11በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች ሁሉ፦ “እኛ ምስክሮች ነን፥ ጌታ ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ፥ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፥ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተልሔም ይጠራ።#ዘፍ. 29፥31—30፥24፤ 35፥16-19። 12ቤትህም ጌታ ከዚህች ቈንጆ ከሚሰጥህ ዘር ትዕማር ለይሁዳ እንደ ወለደች እንደ ፋሬስ#4፥12 የቦዔዝ ቅድመ አያቶች ቍጥር 18-22 ተመልከት። ቤት ይሁን” አሉት።
የዳዊት የትውልድ ሐረግ
13ቦዔዝም ሩትን ወሰደ፥ ሚስትም ሆነችው፥ ወደ እርሷም ገባ፤ እግዚአብሔርም ፅንስ ሰጣት፥ ወንድ ልጅም ወለደች። 14ሴቶችም ናዖሚንን፦ “ዛሬ ዋርሳ ያላሳጣሽ ጌታ ይባረክ፥ ስሙም በእስራኤል ይጠራ። 15ምራትሽ በጣም ትወድሻለች፤ ሰባት ልጆች ከሚያደርጉልሽ የበለጠ አድርጋልሻለች፤ አሁን ደግሞ ሕይወትሽን የሚያድስልሽና በእርጅናሽ ወራት የሚጦርሽን ወንድ ልጅ ወልዳልሻለች።” 16ናዖሚም ሕፃኑን ወሰደች አቀፈችውም፥ ሞግዚትም ሆነችው። 17የጐረቤት ሴቶች ልጁን “ኢዮቤድ” ብለው ስም አወጡለት፤ “ለናዖሚ ወንድ ልጅ ተወለደላት!” እያሉም ለሰው ሁሉ አወሩ። የንጉሥ ዳዊት አባት የሆነውን እሴይን የወለደ ይኸው ኢዮቤድ ነው።
የዳዊት የዘር ሐረግ#ሉቃ. 1፥58። 18የፋሬስም ትውልድ ይህ ነው፥ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፥#1ዜ.መ. 2፥4-15፤ ማቴ. 1፥3-6።#ዘፍ. 46፥12፤ ዘኍ. 26፥21፤ 1ዜ.መ. 4፥1። 19ኤስሮምም አራምን ወለደ፥ አራምም አሚናዳብን ወለደ፥ 20አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፥ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፥ 21ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፥#ዘፀ. 6፥23፤ ዘኍ. 1፥7፤ 2፥3፤ 7፥12-17፤ 10፥14። 22ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፥ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፥ እሴይም ዳዊትን ወለደ።#1ሳሙ. 16፥2-13።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሩት 4: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: