መዝሙረ ዳዊት 17
17
1የዳዊት ጸሎት።
#
መዝ. 26፥2፤ 139፥23። አቤቱ፥ ጽድቄን ስማ ጩኸቴንም አድምጥ፥
ተንኰል ከሌለበት ከንፈር የሚወጣውንም ጸሎቴን አድምጥ።
2ፍርዴ ከፊትህ ይውጣ፥
ዐይኖችህም በቅንነት ይዩ።
3ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፥
ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም።
4የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፥
ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።
5 #
መዝ. 18፥36፤ ኢዮብ 23፥11-12። እግሮች እንዳይናወጡ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።
6አቤቱ፥ ሰምተኸኛልና ወደ አንተ ጠራሁ፥
ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ ቃሌንም ስማ።
7የሚያምኑህን ከሚቃወሙ በቀኝህ የምታድናቸው፥
ቸርነትህን ድንቅ አድርገህ ግለጠው።
8እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፥
በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ
9 #
መዝ. 10፥9፤ 22፥14፤ 22፤ 35፥17፤ 58፥7፤ ኢዮብ 4፥10-11። ከሚያስጨንቁኝ ከኃጢአተኞች፥
ነፍሴንም ከሚከብቡአት ከጠላቶቼ።#መዝ. 36፥8፤ 57፥2፤ 61፥5፤ 63፥8፤ 91፥4፤ ዘዳ. 32፥10፤ ሩት 2፥12፤ ዘካ. 2፥12፤ ማቴ. 23፥37።
10አንጀታቸውን በስብ ቋጠሩ፥
በአፋቸውም ትንቢትን ተናገሩ።
11አሁንም እርምጃችንን ከበቡ፥
ዓይናቸውን ወደ ምድር ዝቅ ዝቅ አደረጉ።
12እርሱ ንጥቂያን እንደሚናፍቅ አንበሳ
ተሸጉጦም እንደሚኖር እንደ አንበሳ ደቦል ነው።
13አቤቱ፥ ተነሥ፥ ቀድመህ ወደ ታች ጣለው፥
ነፍሴን ከኃጢአተኛ በሰይፍህ አድናት።
14አቤቱ፥ ከሰዎች፥
እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች
ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥
ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥
ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል
የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።
15 #
መዝ. 4፥7፤ 31፥17፤ 67፥2፤ 80፥4፤ ዘኍ. 6፥25፤ ዳን. 9፥17። እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፥
ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 17: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in