YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 18

18
1ለመዘምራን አለቃ ከሳኦል እጅና ከጠላቶቹ ሁሉ እጅ ጌታ ባዳነው ቀን በዚህ መዝሙር ቃል ለጌታ የተናገረው የጌታ ባርያ የዳዊት መዝሙር። 2እንዲህም አለ፦
# 2ሳሙ. 22፥2-51። አቤቱ ጉልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ።
3 # መዝ. 3፥4፤ 31፥3-4፤ 42፥10፤ ዘፍ. 49፥24፤ ዘዳ. 32፥4። ጌታ ዓለቴ፥ አምባዬ፥ መድኃኒቴ፥
አምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ዓለቴ፥
ጋሻዬ፥ የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው።
4ምስጋና የሚገባውን ጌታን እጠራለሁ፥
ከጠላቶቼም እድናለሁ።
5የሞት ገመዶች ጠፍረው ያዙኝ፥
የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ፥
6 # መዝ. 88፥8፤ 93፥3-4፤ 116፥3-4። የሲኦል ገመዶች ተበተቡኝ፥
የሞት ወጥመዶችም ደረሱብኝ።
7 # ዮናስ 2፥3። በጨነቀኝ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፥
ወደ አምላኬም ጮኽሁ፥
ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥
ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።
8 # መዝ. 97፥3-4፤ 99፥1፤ መሳ. 5፥4-5፤ ኢሳ. 64፥1፤ ዕብ. 3፥9-11። ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፥
የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ ተናጉም
እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና።
9ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፥ ከአፉም የሚበላ እሳት ነደደ፥
ፍምም ከእርሱ በራ።
10 # መዝ. 104፥3፤ 144፥5፤ ኢሳ. 63፥19። ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም፥
ጨለማ ከእግሩ በታች ነበረ።
11በኪሩቤልም ሠረገላ ላይ ተቀምጦ በረረ፥
በነፋስም ክንፍ አንዣበበ።
12መሰወሪያውን ጨለማ አደረገ፥
በዙሪያውም ድንኳኑ፥
በውሃ የተሞሉ ጥቁር ደመናዎች ሸፍነውታል።
13 # ዘፀ. 13፥21፤ 19፥16። በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ ደመናትና በረዶ
የእሳት ፍምም አለፉ።
14 # መዝ. 29፤ 77፥19፤ ዘፀ. 19፥19፤ ኢዮብ 37፥3-4። ጌታ ከሰማያት አንጐደጐደ፥
ልዑልም ቃሉን ሰጠ። በረዶና የእሳት ፍምም፤
15 # መዝ. 144፥6፤ ጥበ. 5፥21። ፍላጻውን ላከ በተናቸውም፥
መብረቆችን አበዛ አወካቸውም።
16 # መዝ. 77፥17፤ ዘካ. 9፥14። አቤቱ፥ ከዘለፋህ
ከአፍንጫህ እስትንፋስ የተነሣ፥
የውኆች ምንጮች ታዩ፥
የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ።
17 # መዝ. 144፥7። ከላይ ሰደደ ወሰደኝም፥
ከብዙ ውኆችም አወጣኝ።
18ከብርቱዎች ጠላቶቼ
ከሚጠሉኝም አዳነኝ፥ በርትተውብኝ ነበርና።
19በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፥
ጌታ ግን ድጋፍ ሆነኝ።
20ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፥
ወድዶኛልና አዳነኝ።
21 # መዝ. 26፤ 1ሳሙ. 26፥23። ጌታ እንደጽድቄ ይከፍለኛል፥
እንደ እጄ ንጽሕና ይመልስልኛል።
22የጌታን መንገድ ጠብቄአለሁና፥
በአምላኬም አላመፅሁም።
23ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበረና፥
ሥርዓቱንም ከፊቴ አላራቅሁም።
24በእርሱ ዘንድ ቅን ነበርሁ፥
ከኃጢአቴም ተጠበቅሁ።
25ጌታም እንደጽድቄ
እንደ እጄም ንጽሕና በዐይኖቹ ፊት መለሰልኝ።
26 # መዝ. 125፥4። ከታማኝ ሰው ጋር ታማኝ ሆነህ ትገኛለህ፥
ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፥
27ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፥
ከጠማማም ጋር ብልህ ሆነህ ትገኛለህ።
28 # ኢዮብ 22፥29፤ ምሳ. 3፥34። አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥
የትዕቢተኞችን ዐይን ግን ታዋርዳለህ።
29 # መዝ. 27፥1፤ 36፥10፤ 43፥3፤ 119፥105፤ ኢዮብ 29፥3፤ ሚክ. 7፥8። አንተ መብራቴን ታበራለህና፥
ጊታ አምላኬ ጨለማዬን ያበራል።
30በአንተ ግብረ ኃይል አጠቃለሁ፥
በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁ።
31 # መዝ. 12፥6፤ 77፥13፤ ምሳ. 30፥5። የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥
የጌታም ቃል የነጠረ ነው፥
በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው።
32 # ኢሳ. 44፥8፤ 45፥21። ከጌታ በቀር አምላክ ማን ነው?
ከአምላካችን በቀር አምላክ ማን ነው?
33ኃይልን የሚያስታጥቀኝ መንገዴንም የሚያቃና፥
34 # ዕን. 3፥19። እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች የሚያበረታ
በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው።
35 # መዝ. 144፥1። እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፥
በክንዴም የናስ ቀስት እገትራለሁ።
36ለደኅንነቴም ጋሻን ሰጠኸኝ፥
ቀኝህም ትረዳኛለች፥
ትምህርትህም አሳደገችኝ፥
37 # መዝ. 17፥5። አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥
እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
38ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ እይዛቸዋለሁም፥
እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም።
39አስጨንቃቸዋለሁ፥ መቆምም አይችሉም፥
ከእግሬም በታች ይወድቃሉ።
40ለጦርነት ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፥
በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ።
41የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥
የሚጠሉኝንም አጠፋቸዋለሁ።
42ጮኹ የሚረዳቸውም አልነበረም፥
ወደ ጌታ ጮኹ፥ ነገር ግን አልመለሰላችውም።
43እንደ ትቢያ በነፋስ ፊት እፈጫቸዋለሁ፥
እንደ አደባባይም ጭቃ እረግጣቸዋለሁ።
44ከሕዝብ ክርክር ታድነኛለህ፥
የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥
የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል።
45በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ፥
የባዕድ ልጆች ያጐነብሱልኛል።
46 # ሚክ. 7፥17። የባዕድ ልጆች ጠወለጉ፥
በመንቀጥቀጥም ከምሽጋቸው ወጥተው
ወደ እኔ መጡ።
47 # መዝ. 144፥1። ጌታ ሕያው ነው፥ አምላኬም መጠጊያዬ ቡሩክ ነው፥
የመድኃኒቴም አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።
48 # መዝ. 144፥2። በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ
አሕዛብን በበታቼ ያስገዛልኛል።
49ከጠላቶቼ የሚታደገኝ እርሱ ነው፥
በእኔም ላይ ከቆሙት በላይ ታደርገኛለህ፥
ከግፈኛ ሰው ታድነኛለህ።
50 # መዝ. 7፥18፤ 30፥5፤ 57፥9፤ 135፥3፤ 146፥2፤ ሮሜ 15፥9። አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥
ለስምህም እዘምራለሁ።
51 # መዝ. 89፥28-37፤ 144፥10፤ 1ሳሙ. 2፥10። የንጉሡን መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፥
ቸርነቱንም ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ ለዘለዓለም ይሰጣል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in