YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 26

26
1የዳዊት መዝሙር።
# መዝ. 7፥9። አቤቱ፥ እኔ በቅንነት ሄጃለሁና ፍረድልኝ፥
በጌታም አምኛለሁና አልናወጥም።
2 # መዝ. 17፥3፤ 139፥23። አቤቱ፥ ፈትነኝ መርምረኝም፥
ኩላሊቴንና ልቤን መርምር።
3 # መዝ. 86፥11። ቸርነትህ በዓይኔ ፊት ነውና፥
በእውነትህም ተመላለስሁ።
4ከአታላዮች ጋር አልተቀመጥሁም፥
ከአስመሳዮችም ጋር አልገባሁም።
5የክፉ አድራጊዎቸን ማኅበር ጠላሁ፥
ከክፉዎችም ጋር አልቀመጥም።
6 # መዝ. 73፥13። እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፥
አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥
7የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፥
ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ።
8 # መዝ. 29፥9፤ 63፥3፤ ዘፀ. 24፥16፤ 25፥8። አቤቱ፥ የቤትህን ስፍራ
የክብርህንም ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።
9 # መዝ. 28፥3። ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥
ከደም ሰዎችም#26፥9 ነፍሰ ገዳዮች ጋር ሕይወቴን አታጥፋ።
10በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥
ቀኛቸውም በጉቦ ተሞልታለች።
11 # መዝ. 101፥6፤ መዝ. 25፥16። እኔ ግን በቅንነት ሄጃለሁ፥
አድነኝ ማረኝም።
12 # መዝ. 22፥23፤ 35፥18፤ 149፥1። እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና፥
አቤቱ፥ በማኅበር አመሰግንሃለሁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in