YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 46

46
1ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ምሥጢር፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
2 # መዝ. 48፥4፤ ኢሳ. 33፥2። አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥
ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።
3ስለዚህ ምድር ብትለዋወጥ፥
ተራሮችም በባሕር ልብ ውስጥ ቢናወጡ አንፈራም።
4 # መዝ. 93፥3-4፤ ኢዮብ 9፥5-6፤ ኢሳ. 24፥18-20፤ 54፥10። ውኆቻቸው እየገነፈሉ ጮኹ፥
ተራሮችም ከኃይሉ የተነሣ ተንቀጠቀጡ።
5 # መዝ. 48፥2-3፤ 76፥3። የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛሉ፥
ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።
6 # ኢሳ. 7፥14። እግዚአሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም፥
እግዚአብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል።
7 # መዝ. 2፥1-5፤ 48፥5-8፤ 76፥7-9፤ ኢሳ. 17፥12-14። አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተረበሹ፥
እርሱ ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች።
8የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፥
የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።
9 # መዝ. 48፥9-10። የጌታን ሥራ፥
በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ።
10 # መዝ. 76፥4። እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነትን ያስቆማል፥
ቀስትን ይሰብራል፥ ጦርንም ይቆራርጣል፥
በእሳትም ጋሻን ያቃጥላል።
11 # መዝ. 48፥11። ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንሁ እወቁ፥
በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥
በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።
12የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፥
የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in