YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 53

53
1ለመዘምራን አለቃ፥ በማኽላት፥ የዳዊት ትምህርት።
2 # መዝ. 14፥1-5። ኣላዋቂ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል።
ረከሱ በበደላቸውም ጐሰቈሉ፥
በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም።#መዝ. 10፥4፤ 36፥2፤ ኢሳ. 32፥6፤ ኤር. 5፥12፤ ሮሜ 3፥10-12።
3 # መዝ. 11፥4፤ 102፥20። የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ
እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
4 # መዝ. 12፥2። ሁሉም በደሉ፥ አብረውም ረከሱ፥
አንድ እንኳ በጎን ነገር የሚያደርጋት የለም።
5 # መዝ. 27፥2፤ መዝ. 79፥6፤ ኢሳ. 9፥11። እንጀራ እንደሚበላ ሕዝቤን የሚበሉ
ግፍ አድራጊዎች ሁሉ አያውቁምን?
እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።
6በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅጉን ፈሩ፥
እግዚአብሔር የከበቡህን አጥንቶች በትኖአልና፥
እግዚአብሔር ንቆአቸዋልና አሳፈርሃቸው።
7 # መዝ. 85፥2። መድኃኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን በሰጠ!
እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥
ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in