መዝሙረ ዳዊት 54
54
1ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት ትምህርት። 2#1ሳሙ. 23፥19፤ 26፥1።ዜፋውያን መጥተው ለሳኦል፦ እነሆ ዳዊት በእኛ ዘንድ ተሸሽጓል ብለው በነገሩት ጊዜ፥
3አቤቱ፥ በስምህ አድነኝ፥
በኃይልህም ፍረድልኝ።
4አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥
የአፌንም ቃል አድምጥ፥
5 #
መዝ. 86፥14። እንግዶች ተነሥተውብኛልና፥
ጨካኞችም ነፍሴን ሽተዋታልና።
እግዚአብሔርን በፊታቸው አላደረጉትም።
6 #
መዝ. 118፥7። እነሆ፥ እግዚአብሔር ይረዳኛል፥
ጌታም ለሕይወቴ ደጋፊ ነው።
7 #
መዝ. 143፥12። ክፋትን ወደ ጠላቶቼ ይመልሳታል፥
በእውነትህም አጥፋቸው።
8በፈቃዴ እሠዋልሃለሁ፥
አቤቱ፥ መልካም ነውና ስምህን አመሰግናለሁ፥
9 #
መዝ. 59፥11፤ 91፥8፤ 92፥12። ከመከራ ሁሉ አድኖኛልና፥
ዓይኔም የጠላቶቼን ውድቀት አይታለችና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 54: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fen.png&w=128&q=75)
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in