መዝሙረ ዳዊት 64
64
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2አቤቱ፥ በሮሮዬ ድምፄን ስማ፥
ከጠላትም ፍርሃት ነፍሴን አድን።
3ከክፉዎች ደባ፥
ከዓመፀኞችም ብዛት ሰውረኝ።
4 #
መዝ. 11፥2፤ 37፥14፤ 55፥22፤ 57፥5። እንደ ሰይፍ ምላሳቸውን አሰሉ፥
እንደ ፍላጻ መራራ ነገርን ለመወርወር፥
5ንጹሕንም በስውር ለመንደፍ ቀስትን ገተሩ፥
ድንገት ይነድፉታል አይፈሩምም።
6ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ፥
ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ፥
ማንስ ያየናል? ይላሉ።
7 #
መዝ. 140፥3፤ ምሳ. 6፥14። ዓመፃን ፈለጓት፥
ሲፈትኑም አለቁ፥
የሰው የውስጥ አሳቡና ልቡ የጠለቀ ነው፥
8 #
መዝ. 7፥13-14፤ 38፥3፤ ዘዳ. 32፥42። እግዚአብሔርም ከፍ ከፍ ይላል።
ድንገተኛ ፍላጻም ያቈስላቸዋል፥
9 #
መዝ. 5፥11፤ 44፥14፤ 52፥6። አንደበታቸው ያሰናክላቸዋል፥
የሚያዩአቸውም ሁሉ ይደነግጣሉ።
10ሰዎች ሁሉ ፈሩ፥
የእግዚአብሔርንም ሥራ ተናገሩ፥
ሥራውንም አስተዋሉ።
11 #
መዝ. 36፥8፤ 57፥2። ጻድቅ በጌታ ደስ ይለዋል፥ በእርሱም ይታመናል፥
ልባቸውም ቅን የሆነ ሁሉ እልል ይላሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 64: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fen.png&w=128&q=75)
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in