YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 90

90
1የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ጸሎት።
አቤቱ፥ አንተ ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን።
2 # መዝ. 48፥15፤ 55፥20፤ 93፥2፤ 102፥13፤ ዕብ. 1፥12። ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥
ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ አንተ ነህ።
3 # መዝ. 103፥14፤ 104፥29፤ 146፥4፤ ዘፍ. 3፥19፤ 1መቃ. 2፥63፤ ኢዮብ 34፥14-15፤ መክ. 3፥20፤ 12፥7፤ ሲራ. 40፥11። ሰውን ወደ አፈር ትመልሳለህ፥
“የሰው ልጆች ሆይ”፥ ተመለሱ ትላለህ፥
4 # 2ጴጥ. 3፥8። ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥
እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓት ነውና።
5 # መዝ. 89፥48። ታጥለቀልቃቸዋለህ፥ እንደ ሕልም ናቸው፥
በማለዳም እንደሚያልፍ ሣር።
6 # መዝ. 37፥2፤ 102፥11፤ 103፥15-16፤ ኢዮብ 14፥1-2፤ ኢሳ. 40፥6-8። ማልዶ ያብባል፥
በሠርክም ጠውልጎና ደርቆ ይወድቃል።
7እኛ በቁጣህ አልቀናልና፥
በመዓትህም ደንግጠናልና።
8 # መዝ. 109፥14-15፤ ሆሴዕ 7፥2። የተሰወረውን መተላለፋችንን በፊትህ ብርሃን፥
ምሥጢራችንን በፊትህ አስቀመጥህ።
9 # መዝ. 39፥5-7፤ 62፥10፤ 102፥24-25፤ 144፥4፤ ዘፍ. 6፥3፤ ኢዮብ 7፥6፤16፤ 14፥5፤ ምሳ. 10፥27፤ መክ. 6፥12፤ ጥበ. 2፥5፤ ሲራ. 18፥8፤ ኢሳ. 65፥20። ዘመናችን ሁሉ አልፎአልና፥
እኛም በመዓትህ አልቀናልና፥
ዘመኖቻችንንም እንደ ትንፋሽ#90፥9 የሰባ ሊቃናት “እንደ ሸረሪት ድር” ይላል። ይሆናሉ።
10የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥
ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው፥
ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፥
ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ እኛም እንጠፋለንና።
11የቁጣህን ጽናት ማን ያውቃል?
የቁጣህንስ ግርማ ማን ያውቃል?
12በልብ ጥበብን እንድንማር፥
ቀኖቻችንን እንዴት እንደምንቆጥር እንዲህ አስታውቀን።
13አቤቱ፥ ተመለስ፥ እስከ መቼስ ነው?
ለአገልጋዮችህ ራራ።
14 # መዝ. 17፥15። በማለዳ ጽኑ ፍቅርህን እንጠግባለን፥
በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን።
15 # ዘኍ. 14፥34፤ ኤር. 31፥13። መከራ ባሳየኸን ዘመን ፈንታ፥
ክፉም ባየንባቸው ዘመኖች ፋንታ ደስ አሰኘን።
16ሥራህ ለአገልጋዮችህ ይታይ፥
ግርማህም ለልጆቻቸው ይሁን።
17 # መዝ. 33፥22። የጌታ አምላካችን ቸርነት#90፥17 የሰባ ሊቃናት “ብርሃን” ይላል። በላያችን ይሁን።
የእጆቻችንንም ሥራ በላያችን አቅና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in