መዝሙረ ዳዊት 91
91
1በልዑል መጠጊያ የሚኖር
ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።
2 #
መዝ. 18፥3፤ 31፥3-4፤ 42፥10፤ 142፥6፤ 2ሳሙ. 22፥3። ጌታን፦ “አንተ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ ነህ እለዋለሁ”፥
የምታመንበት አምላኬ ነውና።
3እርሱ ከአዳኝ#91፥3 “ከተሰወረ ወጥመድ” የሚሉ ትርጉሞችም አሉ። ወጥመድ
ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።
4 #
መዝ. 17፥8፤ 36፥8፤ 57፥2፤ 63፥8፤ ዘዳ. 32፥11፤ ሩት 2፥12፤ ማቴ. 23፥37። በላባዎቹ ይጋርድሃል፥
ከክንፎቹም በታች ትጠለላለህ፥
ታማኝነቱ እንደ ጋሻና እንደ ቅጥር ይከብብሃል።
5 #
ምሳ. 3፥25፤ መኃ. መኃ. 3፥8። ከሌሊት ሽብር፥
በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥
6 #
ዘዳ. 32፥24። በጨለማ ከሚጓዝ መቅሰፍት፥
በቀትር ከሚደመስስ አደጋ አትፈራም።
7በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም ዐሥር ሺህ ይወድቃሉ፥
ወደ አንተ የሚጠጋ የለም።
8 #
መዝ. 92፥12። በዐይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥
የኃጥኣንንም ቅጣት ታያለህ።
9ጌታን፥ “አንተ ተስፋዬ ነህ” ብለህ፥
ልዑልን መጠጊያህ አድርገሃልና።
10 #
ምሳ. 12፥21፤ ዘዳ. 7፥15። ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥
መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።
11 #
ማቴ. 4፥6፤ ሉቃ. 4፥10። በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ
መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፥#ዕብ. 1፥14።
12 #
መዝ. 121፥3፤ ምሳ. 3፥23። እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል
በእጆቻቸው ያነሡሃል።
13 #
ኢሳ. 11፥8፤ ሉቃ. 10፥19። በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፥
አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
14 #
መዝ. 9፥11፤ 119፥132። በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፥
ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ#91፥14 ዕብራይስጡ “ከፍ አደርገዋለሁ” ይላል። ።
15 #
ኢሳ. 43፥2፤ ኤር. 33፥3፤ ዘካ. 13፥9። ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥
በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፥
አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
16 #
ምሳ. 3፥2። ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥
ማዳኔንም አሳየዋለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 91: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in