መዝሙረ ዳዊት 95
95
የዳዊት ምስጋና መዝሙር
1ኑ፥ በጌታ ደስ ይበለን፥
ለመዳናችን ዓለት እልል እንበል።
2በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ፥
በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል፥
3 #
መዝ. 47፥3፤ 135፥5። ጌታ ታላቅ አምላክ ነውና፥
በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና።
4የምድር ዳርቻዎችም በእጁ ውስጥ ናቸው፥
የተራሮች ከፍታዎች የእርሱ ናቸው።
5 #
መዝ. 24፥1-2። ባሕር የእርሱ ናት እርሱም ፈጠራት፥
የብስንም እጆቹ ሠሩአት።
6ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፥
በፈጠረን በእርሱ በጌታ ፊት እንበርከክ፥
7 #
መዝ. 81፥8፤ 106፥32፤ ዕብ. 3፥7-11፤15፤ 4፥3፤5፤7። እርሱ አምላካችን ነውና፥
እኛ የማሰማርያው ሕዝብ የእጁም በጎች ነንና።#መዝ. 23፥1-3፤ 100፥3፤ ሚክ. 7፥14።
8በምድረ በዳ፥ በመሪባና በማሳ#95፥8 የቦታ ስሞች እንዳደረጋችሁት፥
ልባችሁን አታጽኑ።
9 #
ዘኍ. 14፥22፤ 20፥2-13፤ ዘዳ. 6፥16፤ 33፥8። የተፈታተኑኝ አባቶቻችሁ
ምንም እንኳን ሥራዬን ቢያዩም ፈተኑኝ።
10 #
መዝ. 78፥8፤ ዘኍ. 14፥34፤ ዘዳ. 32፥5። ያችን ትውልድ አርባ ዓመት ተጸየፍኳት፦
ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፥
“እነርሱም መንገዴን አላወቁም” አልሁ።
11“ወደ ዕረፍቴም ጨርሶ አትገቡም” ስል በቁጣዬ ማልሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 95: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in