YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 7

7
1የቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ሰዎ​ችም መጥ​ተው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት አወጡ፤ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም ላይ ወዳ​ለው ወደ አሚ​ና​ዳብ ቤት አገ​ቡ​አት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት እን​ዲ​ጠ​ብቅ ልጁን አል​ዓ​ዛ​ርን ቀደ​ሱት። 2ታቦ​ቲ​ቱም በቂ​ር​ያ​ት​ይ​ዓ​ሪም ከተ​ቀ​መ​ጠ​ች​በት ቀን ጀምሮ ወራቱ ረዘመ፤ ሃያ ዓመ​ትም ሆነ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ተለ።
ሳሙ​ኤል የእ​ስ​ራ​ኤል መሪ ስለ​መ​ሆኑ
3ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሁሉ፥ “በሙሉ ልባ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​መ​ለ​ሳ​ችሁ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክ​ትና ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አርቁ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅኑ፤ እር​ሱ​ንም ብቻ አም​ልኩ፤ እር​ሱም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ያድ​ና​ች​ኋል” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው። 4የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የበ​ዓ​ሊ​ምን አማ​ል​ክ​ትና የአ​ስ​ጣ​ሮ​ትን ምስ​ሎች አራቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ብቻ አመ​ለኩ።
5ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ወደ መሴፋ#ዕብ. “ምጽጳ” ይላል። ሰብ​ስቡ፤ ስለ እና​ን​ተም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጸ​ል​ያ​ለሁ” አለ። 6እነ​ር​ሱም ወደ መሴፋ ተሰ​በ​ሰቡ፤ ውኃም ቀድ​ተው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በም​ድር ላይ አፈ​ሰሱ፤ በዚ​ያም ቀን ጾሙ፤ በዚ​ያም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በድ​ለ​ናል” አሉ። ሳሙ​ኤ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ በመ​ሴፋ ፈረደ። 7ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ተሰ​በ​ሰቡ በሰሙ ጊዜ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዘመቱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሰም​ተው ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ፈሩ። 8የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ ከመ​ጮኽ ዝም አት​በል። እር​ሱም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ያድ​ነ​ናል” አሉት። 9ሳሙ​ኤ​ልም አንድ የበግ ጠቦት ወስዶ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ ከሕ​ዝቡ ጋር አቀ​ረ​በው፤ ሳሙ​ኤ​ልም ስለ እስ​ራ​ኤል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው። 10ሳሙ​ኤ​ልም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ሲያ​ሣ​ርግ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ሊዋጉ ቀረቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያች ቀን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ታላቅ የነ​ጐ​ድ​ጓድ ድምፅ አን​ጐ​ደ​ጐደ፤ ደነ​ገ​ጡም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ፊት ድል ተመቱ። 11የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከመ​ሴፋ ወጡ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም አሳ​ደዱ፤ በቤ​ኮር ታችም እስ​ኪ​ደ​ርሱ ድረስ መቱ​አ​ቸው።
12ሳሙ​ኤ​ልም አንድ ድን​ጋይ ወስዶ በመ​ሴ​ፋና በአ​ሮ​ጌው ከተማ መካ​ከል#ዕብ. “በም​ጽ​ጳና በሼን መካ​ከል” ይላል። አኖ​ረው፤ ስሙ​ንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ቶ​ናል” ሲል “አቤ​ን​ኤ​ዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድ​ኤት ማለት ነው። 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አዋ​ረ​ዳ​ቸው፤ ዳግ​መ​ኛም ከዚያ ወዲያ ወደ እስ​ራ​ኤል ድን​በር አል​ወ​ጡም፤ በሳ​ሙ​ኤ​ልም ዘመን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ነበ​ረች። 14ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከአ​ስ​ቀ​ሎና ጀምሮ እስከ፤ ጌት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አዞብ” ይላል። ድረስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የወ​ሰ​ዱ​አ​ቸው ከተ​ሞች ለእ​ስ​ራ​ኤል ተመ​ለሱ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ድን​በ​ሩን ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ወሰዱ። በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በአ​ሞ​ራ​ው​ያን መካ​ከ​ልም ሰላም ሆነ።
15ሳሙ​ኤ​ልም በዘ​መኑ ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርድ ነበር። 16በየ​ዓ​መ​ቱም ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌል​ጌ​ላና ወደ መሴፋ ይዞር ነበር፤ በእ​ነ​ዚ​ያም በተ​ቀ​ደሱ ስፍ​ራ​ዎች ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርድ ነበር። 17ቤቱም በዚያ ነበ​ረና ወደ አር​ማ​ቴም ይመ​ለስ ነበር፤ በዚ​ያም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርድ ነበር፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in