YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 1

1
ሰላ​ም​ታና ምስ​ጋና
1 # የሐዋ. 18፥1። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሐዋ​ርያ ከሆነ ጳው​ሎ​ስና ከወ​ን​ድ​ማ​ችን ጢሞ​ቴ​ዎስ በቆ​ሮ​ን​ቶስ ሀገር ላለ​ችው የእ​ግ​ዚ​አ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንና በአ​ካ​ይያ ሀገር ላሉ ቅዱ​ሳን ሁሉ፥ 2ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።
3የም​ሕ​ረት አባት፥ የመ​ጽ​ና​ና​ትም ሁሉ አም​ላክ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን። 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ጽ​ና​ናን በዚያ መጽ​ና​ናት በመ​ከራ ያሉ​ትን ሁሉ ማጽ​ና​ናት እን​ችል ዘንድ ከመ​ከ​ራ​ችን ሁሉ ያጽ​ና​ናን እርሱ ይመ​ስ​ገን። 5የክ​ር​ስ​ቶስ መከራ በእኛ ላይ እንደ በዛ መጠን እን​ዲሁ መጽ​ና​ና​ታ​ች​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ ይበ​ዛ​ልና። 6መከራ ብን​ቀ​በ​ልም እና​ንተ እን​ድ​ት​ድ​ኑና እን​ድ​ት​ጽ​ናኑ ነው፤ ብን​ጽ​ና​ናም እኛ የተ​ቀ​በ​ል​ነ​ውን ያን መከራ በመ​ታ​ገሥ ስለ​ሚ​ደ​ረግ መጽ​ና​ና​ታ​ችሁ ነው። 7ስለ እና​ንተ ያለን ተስ​ፋም የጸና ነው፤ መከ​ራ​ች​ንን እንደ ተካ​ፈ​ላ​ችሁ መጠን፥ እን​ዲሁ በመ​ጽ​ና​ና​ታ​ች​ንም እን​ደ​ም​ት​ተ​ባ​በሩ እና​ው​ቃ​ለን።
8 # 1ቆሮ. 15፥3። ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በእ​ስያ መከራ እንደ ተቀ​በ​ልን ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ፤ ለሕ​ይ​ወ​ታ​ችን ተስፋ እስ​ክ​ን​ቈ​ርጥ ድረስ ከዐ​ቅ​ማ​ችን በላይ እጅግ መከራ ጸን​ቶ​ብን ነበ​ርና። 9ሙታ​ንን በሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንጂ በራ​ሳ​ችን እን​ዳ​ን​ታ​መን በው​ስ​ጣ​ችን ለመ​ሞት ቈር​ጠን ነበር። 10እር​ሱም እን​ዲህ ካለ ሞት አዳ​ነን፤ ያድ​ነ​ን​ማል፤ አሁ​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ድ​ነን እር​ሱን እን​ታ​መ​ና​ለን። 11በብ​ዙ​ዎች ጸሎት ጸጋን እና​ገኝ ዘንድ፥ ብዙ​ዎ​ችም በእኛ ፋንታ ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ እና​ንተ በጸ​ሎ​ታ​ችሁ ርዱን።
12በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ትና ይቅ​ርታ መመ​ኪ​ያ​ች​ንና የነ​ፃ​ነ​ታ​ችን ምስ​ክር ይህቺ ናትና፥ በሥ​ጋዊ ጥበብ ሳይ​ሆን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይል​ቁ​ንም በእ​ና​ንተ ዘንድ ተመ​ላ​ለ​ስን። 13የም​ታ​ነ​ቡ​ት​ንና የም​ታ​ው​ቁ​ትን ነው እንጂ፥ ሌላ የም​ን​ጽ​ፍ​ላ​ችሁ የለ​ምና፥ ይህ​ንም እስከ ፍጻሜ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ው​ሉት ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ። 14እኛ መመ​ኪ​ያ​ችሁ እን​ደ​ሆን፥ እን​ዲሁ እና​ን​ተም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቀን መመ​ኪ​ያ​ችን እን​ድ​ት​ሆኑ በከ​ፊል እን​ዳ​ወ​ቃ​ችሁ ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።
15በዚ​ህም ታምኜ ጸጋን በዕ​ጥፍ እን​ድ​ታ​ገኙ በመ​ጀ​መ​ሪያ ወደ እና​ንተ እመጣ ዘንድ መከ​ርሁ። 16#የሐዋ. 19፥21። በእ​ና​ን​ተም በኩል ወደ መቄ​ዶ​ንያ እን​ዳ​ልፍ፥ ዳግ​መ​ኛም ከመ​ቄ​ዶ​ንያ እን​ድ​መ​ለ​ስና እና​ን​ተም ደግሞ ወደ ይሁዳ ሀገር ትሸ​ኙኝ ዘንድ መከ​ርሁ። 17እን​ግ​ዲህ ይህን የመ​ከ​ርሁ በውኑ የሠ​ራ​ሁት እንደ አላ​ዋቂ ሰው ሆኜ ነውን? ወይስ በእኔ በኩል አዎን አዎን፥ አይ​ደ​ለም አይ​ደ​ለም ማለት እን​ዲ​ሆን ያን የም​መ​ክ​ረው ለሰው ይም​ሰል ነውን? 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው፤ ለእ​ና​ን​ተም የሚ​ነ​ገ​ረው ቃላ​ችን እው​ነ​ትና ሐሰት አል​ተ​ቀ​ላ​ቀ​ለ​በ​ትም። 19#የሐዋ. 18፥5። እኛ ማለት እኔ ጳው​ሎስ፥ ስል​ዋ​ኖ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎስ የሰ​በ​ክ​ን​ላ​ችሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እው​ነ​ትና ሐሰት አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ስለ እርሱ ያስ​ተ​ማ​ር​ነው እው​ነት ነው። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠው ተስፋ ሁሉ በክ​ር​ስ​ቶስ እው​ነት ሆኖ​አ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር አሜን እን​ላ​ለን። 21ከእ​ና​ንተ ጋር በክ​ር​ስ​ቶስ ስም የሚ​ያ​ጸ​ና​ንና የቀ​ባን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው። 22ደግ​ሞም ያተ​መ​ንና የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ፈለማ በል​ቡ​ና​ችን የሰ​ጠን እርሱ ነው።
23እኔ ለእ​ና​ንተ በመ​ራ​ራት ወደ ቆሮ​ን​ቶስ እን​ዳ​ል​መ​ጣሁ፥ ስለ ራሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ክር አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ። 24ደስ የሚ​ላ​ች​ሁን እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ እን​ረ​ዳ​ች​ኋ​ለን እንጂ እን​ድ​ታ​ምኑ ግድ የም​ን​ላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ም​ነት ቆማ​ች​ኋ​ልና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in