ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 13
13
ቅዱስ ጳውሎስ ሦስተኛ ጊዜ ወደ ቆሮንቶስ ስለ መምጣቱ
1 #
ዘዳ. 17፥6፤ 19፥15። ወደ እናንተ ስመጣ እነሆ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ነገር ሁሉ፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ የሚጸና አይደለምን? 2ጥንቱን አስቀድሜ ተናግሬአለሁ፤ አሁንም አስቀድሜ እናገራለሁ፤ ቀድሞ ከእናንተ ጋር ሳለሁ እንደ ነገርሁአችሁ፥ አስቀድሞ ለበደሉ፥ ለሌሎችም ሁሉ እንደ ገና የመጣሁ እንደ ሆነ ርኅራኄ እንዳላደርግ፥ እንዲሁ ሳልኖር ለሦስተኛ ጊዜ እናገራለሁ፥ 3ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንደሚናገር ማስረጃ ትሻላችሁና፤ እርሱም ሁሉ የሚቻለው ነው እንጂ፥ በእናንተ ዘንድ የሚሳነው የለም። 4በድካም ተሰቅሎአልና፤ በእግዚአብሔርም ኀይል ሕያው ነውና፤ እኛም ከእርሱ ጋር እንደክማለንና፤ ነገር ግን ስለ እናንተ በሚሆን በእግዚአብሔር ኀይል ከእርሱ ጋር በሕይወት እንኖራለን።
5በሃይማኖት ጸንታችሁ እንደ ሆነ ራሳችሁን መርምሩ፤ እናንተ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር እንዳለ አታውቁምን? እንዲህ ካልሆነ ግን እናንተ የተናቃችሁ ናችሁ። 6እኛም ብንሆን የተናቅን እንዳይደለን እንደምታውቁ እኔ አምናለሁ። 7ምንም ክፉ ሥራ እንዳትሠሩ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ መልካም ነገር እንድታደርጉ ብቻ ነው እንጂ እኛ ደጎች ልንባል አይደለም፤ እኛም እንደ ተናቁ ሰዎች እንሆናለን። 8ለዕውነት ጸንተን እንኖራለን እንጂ፤ ከዕውነት መውጣት አንችልምና። 9እናንተ ትበረቱ ዘንድ እኛ ስንደክም ደስ ይለናል። ጸሎታችንም እናንተ ፍጹማን ትሆኑ ዘንድ ነው።
ሰላምታና ቡራኬ
10ስለዚህም እግዚአብሔር ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ በሰጠን ሥልጣን ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ ቍርጥ ነገር እንዳላደርግባችሁ፥ ሥልጣን እንዳለው ሰው ከእናንተ ጋር ሳልኖር ይህን እጽፋለሁ።
11ወድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ደስ ይበላችሁ፤ ጽኑ፤ ታገሡ፤ በአንድ ልብም ሁኑ፤ በሰላም ኑሩ፤ የሰላምና የፍቅር አምላክም ከእናንተ ጋር ይሁን። 12በተቀደሰ ሰላምታ እርስ በርሳችሁ ሰላም ተባባሉ፤ ቅዱሳን ሁሉ እንዴት ናችሁ? ይሏችኋል። 13የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የመንፈስ ቅዱስም አንድነት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
የመቄዶንያ ክፍል በምትሆን በፊልጵስዩስ ተጽፎ በቲቶና በሉቃስ እጅ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የተላከው ሁለተኛዉ መልእክት ተፈጸመ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ አሜን።
Currently Selected:
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 13: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: