YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 13

13
ቅዱስ ጳው​ሎስ ሦስ​ተኛ ጊዜ ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ስለ መም​ጣቱ
1 # ዘዳ. 17፥6፤ 19፥15። ወደ እና​ንተ ስመጣ እነሆ ይህ ሦስ​ተ​ኛዬ ነው፤ ነገር ሁሉ፥ በሁ​ለት ወይም በሦ​ስት ምስ​ክር አፍ የሚ​ጸና አይ​ደ​ለ​ምን? 2ጥን​ቱን አስ​ቀ​ድሜ ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አሁ​ንም አስ​ቀ​ድሜ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ቀድሞ ከእ​ና​ንተ ጋር ሳለሁ እንደ ነገ​ር​ሁ​አ​ችሁ፥ አስ​ቀ​ድሞ ለበ​ደሉ፥ ለሌ​ሎ​ችም ሁሉ እንደ ገና የመ​ጣሁ እንደ ሆነ ርኅ​ራኄ እን​ዳ​ላ​ደ​ርግ፥ እን​ዲሁ ሳል​ኖር ለሦ​ስ​ተኛ ጊዜ እና​ገ​ራ​ለሁ፥ 3ክር​ስ​ቶስ በእኔ አድሮ እን​ደ​ሚ​ና​ገር ማስ​ረጃ ትሻ​ላ​ች​ሁና፤ እር​ሱም ሁሉ የሚ​ቻ​ለው ነው እንጂ፥ በእ​ና​ንተ ዘንድ የሚ​ሳ​ነው የለም። 4በድ​ካም ተሰ​ቅ​ሎ​አ​ልና፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይል ሕያው ነውና፤ እኛም ከእ​ርሱ ጋር እን​ደ​ክ​ማ​ለ​ንና፤ ነገር ግን ስለ እና​ንተ በሚ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ከእ​ርሱ ጋር በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን።
5በሃ​ይ​ማ​ኖት ጸን​ታ​ችሁ እንደ ሆነ ራሳ​ች​ሁን መር​ምሩ፤ እና​ንተ ራሳ​ች​ሁን ፈትኑ፤ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ዳለ አታ​ው​ቁ​ምን? እን​ዲህ ካል​ሆነ ግን እና​ንተ የተ​ና​ቃ​ችሁ ናችሁ። 6እኛም ብን​ሆን የተ​ና​ቅን እን​ዳ​ይ​ደ​ለን እን​ደ​ም​ታ​ውቁ እኔ አም​ና​ለሁ። 7ምንም ክፉ ሥራ እን​ዳ​ት​ሠሩ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ጸ​ል​ያ​ለን፤ መል​ካም ነገር እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ ብቻ ነው እንጂ እኛ ደጎች ልን​ባል አይ​ደ​ለም፤ እኛም እንደ ተናቁ ሰዎች እን​ሆ​ና​ለን። 8ለዕ​ው​ነት ጸን​ተን እን​ኖ​ራ​ለን እንጂ፤ ከዕ​ው​ነት መው​ጣት አን​ች​ል​ምና። 9እና​ንተ ትበ​ረቱ ዘንድ እኛ ስን​ደ​ክም ደስ ይለ​ናል። ጸሎ​ታ​ች​ንም እና​ንተ ፍጹ​ማን ትሆኑ ዘንድ ነው።
ሰላ​ም​ታና ቡራኬ
10ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ ለማ​ነጽ በሰ​ጠን ሥል​ጣን ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ ቍርጥ ነገር እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ባ​ችሁ፥ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለው ሰው ከእ​ና​ንተ ጋር ሳል​ኖር ይህን እጽ​ፋ​ለሁ።
11ወድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ጽኑ፤ ታገሡ፤ በአ​ንድ ልብም ሁኑ፤ በሰ​ላም ኑሩ፤ የሰ​ላ​ምና የፍ​ቅር አም​ላ​ክም ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን። 12በተ​ቀ​ደሰ ሰላ​ምታ እርስ በር​ሳ​ችሁ ሰላም ተባ​ባሉ፤ ቅዱ​ሳን ሁሉ እን​ዴት ናችሁ? ይሏ​ች​ኋል። 13የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቅር፥ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም አን​ድ​ነት ከሁ​ላ​ችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
የመ​ቄ​ዶ​ንያ ክፍል በም​ት​ሆን በፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ተጽፎ በቲ​ቶና በሉ​ቃስ እጅ ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች የተ​ላ​ከው ሁለ​ተ​ኛዉ መል​እ​ክት ተፈ​ጸመ።
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን፤ አሜን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in