ወደ ገላትያ ሰዎች 1
1
ስለ ጳውሎስ ሹመትና ትምህርት
1በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና ከሙታን ለይቶ በአስነሣው በእግዚአብሔር አብ ነው እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ሐዋርያ ካልሆነ ከጳውሎስ፥ 2አብረውኝ ካሉ ከወንድሞቻችንም፥ በገላትያ ላሉ አብያተ ክርስቲያን፤ 3ከአባታችን ከእግዚአብሔር፥ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን። 4በክፉ ከሚቃወም ከዚህ ዓለም ያድነን ዘንድ በአባታችን በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ኀጢአታችን ራሱን አሳልፎ ሰጠ። 5ለእርሱ ክብር ይሁን፤ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አሜን።
6በጸጋዉ የጠራችሁን ክርስቶስን ከማመን ወደ ልዩ ወንጌል እንዴት ፈጥነው እንዳስወጧችሁ አደንቃለሁ። 7እርሱ ግን ሌላ አይደለም፤ የሚያውኳችሁ ከክርስቶስም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አሉ እንጂ። 8እናንተ ግን የእኛን ፍለጋ ተከተሉ፤#“እናንተ ግን የእኛን ፍለጋ ተከተሉ” የሚለው በግሪኩ የለም። እናንተስ እኛም ብንሆን ወይም መልአክ ከሰማይ ወርዶ እኛ ካስተማርናችሁ ወንጌል ሌላ ቢሰብክላችሁ ውጉዝ ይሁን። 9አስቀድሜ እንደ አልሁ አሁንም ደግሞ እላለሁ፦ ካስተማርናችሁ ሌላ ትምህርት ያስተማራችሁ ቢኖር ውጉዝ ይሁን።
10አሁንስ ለእግዚአብሔር ያይደለ ለሰው ብዬ አስተምራለሁን? ወይስ ሰውን ደስ አሰኛለሁን? ሰውን ደስ ላሰኝ ብወድስ የክርስቶስ ባሪያ አይደለሁም።
ቅዱስ ጳውሎስ ለሐዋርያነት እንደ ተጠራ
11ወንድሞቻችን ሆይ፥ ያስተማርኋችሁ ወንጌል ስለ ሰው እንዳይደለ አስታውቃችኋለሁ። 12ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ገለጠልኝ እንጂ፥ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም፤ አልተማርሁትምም። 13#የሐዋ. 8፥3፤ 22፥4-5፤ 26፥9-11። በአይሁድ ሥርዐት ውስጥ በነበርሁ ጊዜ፥ የነበረውን የቀድሞ ሥራዬን ሰምታችኋል፤ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እጅግ አሳድድና መከራ አጸናባቸው ነበር። 14#የሐዋ. 22፥3። ለአባቶች ሥርዐት እጅግ ቀናተኛ ነበርሁና በወገኖች ዘንድ ከጓደኞች ሁሉ በአይሁድ ዘንድ እጅግ ከበርሁ። 15ከእናቴ ማኅፀን ለይቶ ያወጣኝ እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ በጸጋው ጠራኝ። 16#የሐዋ. 9፥3-6፤ 22፥6-10፤ 26፥13-18። በስሙም ለአሕዛብ ወንጌልን አስተምር ዘንድ፥ በእጄም የልጁ ክብር ይታወቅ ዘንድ#“በእጄም የልጁ ክብር ይታወቅ ዘንድ” የሚለው በግሪኩ የለም። ልጁን ገለጠልኝ፤ ያንጊዜም ከሥጋዊና ከደማዊ ሰው ጋር አልተማከርሁም። 17ከእኔ በፊት ወደ ነበሩት ወደ ሐዋርያትም ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፤ ነገር ግን ወደ ዐረብ ሀገር ሄድሁ፤ ዳግመኛም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ።
መጀመሪያ ወደ ኢየሩሳሌም ስለ መውጣቱ
18 #
የሐዋ. 9፥26-30። ከሦስት ዓመት በኋላ ግን ኬፋን ላየው ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ፤ በእርሱ ዘንድም ዐሥራ አምስት ቀን ሰነበትሁ። 19ነገር ግን የጌታችን ወንድም ያዕቆብን እንጂ ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም። 20ስለምጽፍላችሁም ነገር እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት ሐሰት አልናገርም። 21ከዚህም በኋላ ወደ ሶርያና ወደ ቂልቅያ አውራጃ መጣሁ። 22በክርስቶስም ያሉት የይሁዳ ሀገር ማኅበረ ክርስቲያን ፊቴን አያውቁም ነበር። 23ነገር ግን “ቀድሞ ምእመናንን ያሳድድ የነበረው እርሱ በፊት ያጠፋው የነበረውን የሃይማኖት ትምህርት ዛሬ ይሰብካል” ሲባል ወሬዬን ይሰሙ ነበር። 24ስለ እኔም እግዚአብሔርን ያመሰግኑት ነበር።
Currently Selected:
ወደ ገላትያ ሰዎች 1: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in