YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 6

6
ምግ​ባ​ርን ስለ ማቅ​ናት
1ከእ​ር​ሱም ጋር አብ​ረን እየ​ሠ​ራን፥ የተ​ቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ታ​ደ​ር​ጓት እን​ማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለን። 2#ኢሳ. 49፥8። እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በተ​መ​ረ​ጠ​ችው ቀን ሰማ​ሁህ፤ በመ​ዳ​ንም ቀን ረዳ​ሁህ” እነሆ፥ የተ​መ​ረ​ጠ​ችው ቀን ዛሬ ናት። 3አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ች​ንም እን​ዳ​ይ​ነ​ቀፍ፥ በአ​ን​ዳች ነገር ማሰ​ና​ከያ እን​ዳ​ን​ሰጥ እን​ጠ​ን​ቀቅ። 4ነገር ግን በሁሉ ራሳ​ች​ንን አቅ​ን​ተን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሁን፤ በብዙ ትዕ​ግ​ሥ​ትና በመ​ከራ፥ በች​ግ​ርና በጭ​ን​ቀት ሁሉ፥ 5#የሐዋ. 16፥23። በመ​ገ​ረ​ፍና በመ​ታ​ሰር፥ በድ​ካ​ምና በመ​ታ​ወክ፥ በመ​ት​ጋ​ትና በመ​ጾም፥ 6በን​ጽ​ሕ​ናና በዕ​ው​ቀት፥ በም​ክ​ርና#“በም​ክር” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። በመ​ታ​ገሥ፥ በቸ​ር​ነ​ትና በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ አድ​ልዎ በሌ​ለ​በት ፍቅር፥ 7በእ​ው​ነት ቃል፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ለቀ​ኝና ለግራ በሚ​ሆን የጽ​ድቅ የጦር ዕቃ፥ 8በክ​ብ​ርና በው​ር​ደት፥ በም​ር​ቃ​ትና በር​ግ​ማን፥ እንደ አሳ​ቾች ስን​ታይ እው​ነ​ተ​ኞች ነን። 9እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቁ ስን​ታይ የታ​ወ​ቅን ነን፤ እንደ ሰነ​ፎች ስን​ታ​ይም ልባ​ሞች ነን፤#“እንደ ሰነ​ፎች ስን​ታ​ይም ልባ​ሞች ነን” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። እንደ ሙታን ስን​ታይ ሕያ​ዋን ነን፤ የተ​ቀ​ጣን ስን​ሆ​ንም አን​ገ​ደ​ልም። 10ኀዘ​ን​ተ​ኞች ስን​ሆን ዘወ​ትር ደስ​ተ​ኞች ነን፤ እንደ ድሆች ስን​ሆን ብዙ​ዎ​ችን እና​በ​ለ​ጽ​ጋ​ለን፤ ምንም የሌ​ለን ስን​ሆን ሁሉ በእ​ጃ​ችን ነው።
ስለ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች
11የቆ​ሮ​ን​ቶስ ሰዎች ሆይ፥ ለእ​ና​ንተ አፋ​ችን የተ​ከ​ፈተ ነው፤ ልባ​ች​ንም የሰፋ ነው። 12ከእ​ና​ንተ የደ​ረሰ ኀዘን በእኛ የለም፤ ከእ​ኛም በእ​ና​ንተ ላይ የደ​ረሰ ኀዘን የለም፤ ነገር ግን በል​ባ​ችሁ አዝ​ና​ች​ኋል። 13ልጆች እንደ መሆ​ና​ችሁ፥ ይህን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ ላይ ስለ​ሚ​ገ​ባኝ ብድ​ራቴ እና​ንተ ፍቅ​ራ​ች​ሁን አስ​ፉ​ልኝ።
ከማ​ያ​ምኑ ስለ መለ​የት
14ተጠ​ራ​ጣ​ሪ​ዎች አት​ሁኑ፤#“ተጠ​ራ​ጣ​ሪ​ዎች አት​ሁኑ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ወደ​ማ​ያ​ምኑ ሰዎች አን​ድ​ነ​ትም አት​ሂዱ፤ ጽድ​ቅን ከኀ​ጢ​አት ጋር አንድ የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት ማን ነው? ብር​ሃ​ን​ንስ ከጨ​ለማ ጋር የሚ​ቀ​ላ​ቅል ማን ነው? 15ክር​ስ​ቶ​ስን ከቤ​ል​ሆር ጋር አንድ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ማን ነው? ወይስ ምእ​መ​ና​ንን ከመ​ና​ፍ​ቃን ጋር አንድ ወገን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው ማን ነው? 16#ዘሌ. 26፥12፤ ሕዝ. 37፥27፤ 1ቆሮ. 3፥16፤ 6፥19። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦ​ትስ#ግሪኩ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መቅ​ደስ ከጣ​ዖት ጋር አንድ የሚ​ያ​ደ​ርግ ማን ነው” ይላል። በጣ​ዖት ቤት ውስጥ የሚ​ያ​ኖር ማን ነው? የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያ​ዎች እኛ አይ​ደ​ለ​ን​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “እኔ በእ​ነ​ርሱ አድ​ራ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እኖ​ራ​ለሁ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል።” 17#ኢሳ. 52፥11። ስለ​ዚ​ህም “ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተለ​ይ​ታ​ችሁ ውጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩ​ሳ​ንም አት​ቅ​ረቡ፥ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ። 18#2ሳሙ. 7፥14፤ 1ዜ.መ. 17፥13፤ ኢሳ. 43፥6፤ ኤር. 31፥9። አባት እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ አለ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Free Reading Plans and Devotionals related to ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 6

YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy