YouVersion Logo
Search Icon

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 25

25
ፊስ​ጦስ ስለ መም​ጣ​ቱና ስለ አይ​ሁድ ልመና
1ፊስ​ጦ​ስም ወደ ቂሣ​ርያ ደርሶ ሦስት ቀን ሰነ​በተ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ። 2ሊቃነ ካህ​ና​ትና የአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሎ​ችም ከበ​ቡት፤ የጳ​ው​ሎ​ስ​ንም ነገር ነገ​ሩት። 3ልኮም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ እን​ዲ​ያ​ስ​መ​ጣ​ውና እን​ዲ​ሰ​ጣ​ቸው ለመ​ኑት፤ እነ​ርሱ ግን ወደ​ዚያ ሄደው በመ​ን​ገድ ሸም​ቀው ሊገ​ድ​ሉት ፈል​ገው ነበር። 4ፊስ​ጦ​ስም ጳው​ሎ​ስን በቂ​ሣ​ርያ እን​ደ​ሚ​ጠ​ብ​ቁት፥ እር​ሱም ራሱ ወደ​ዚ​ያው በቶሎ እን​ደ​ሚ​ሄድ መለ​ሰ​ላ​ቸው። 5አይ​ሁ​ድ​ንም፥ “ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ የሚ​ችሉ ካሉ ከከ​ሰ​ሳ​ች​ሁት ከዚያ ሰው ጋር እን​ዲ​ከ​ራ​ከሩ ከእኔ ጋር ይው​ረዱ” አላ​ቸው።
6ስም​ንት ወይም ዐሥር ቀን በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ከሰ​ነ​በተ በኋላ ወደ ቂሣ​ርያ ሄደ፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም በፍ​ርድ ወን​በር ተቀ​ምጦ ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘዘ። 7ጳው​ሎ​ስም በቀ​ረበ ጊዜ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የወ​ረዱ አይ​ሁድ ከብ​በ​ውት ቆሙ፤ ሊረቱ በማ​ይ​ች​ሉ​በ​ትም ብዙና ከባድ ክስ ከሰ​ሱት። 8ጳው​ሎ​ስም ሲመ​ልስ፥ “በአ​ይ​ሁድ ሕግ ላይ ቢሆን፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ላይ ቢሆን፥ በቄ​ሣር ላይም ቢሆን አን​ዳች የበ​ደ​ል​ሁት የለም” አለ። 9ፊስ​ጦስ ግን አይ​ሁድ እን​ዲ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑት ወዶ ጳው​ሎ​ስን፥ “ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጥ​ተህ ስለ​ዚህ ነገር በዚያ ከእኔ ዘንድ ልት​ከ​ራ​ከር ትሻ​ለ​ህን?” አለው። 10ጳው​ሎ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፤ “እኔ ወደ ቄሣር ዙፋን ችሎት እቀ​ር​ባ​ለሁ፤ ፍር​ዴም በዚያ ሊታ​ይ​ልኝ ይገ​ባል፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ላይ የበ​ደ​ል​ሁት በደል እን​ደ​ሌ​ለኝ ከሰው ሁሉ ይልቅ አንተ ራስህ ታው​ቃ​ለህ። 11ከበ​ደ​ልሁ ወይም ለሞት የሚ​ያ​በ​ቃኝ የሠ​ራ​ሁት ክፉ ሥራ ካለ ሞት አይ​ፈ​ረ​ድ​ብኝ አል​ልም፤ ነገር ግን እነ​ዚህ በደል የሌ​ለ​ብ​ኝን በከ​ንቱ የሚ​ከ​ስ​ሱኝ ከሆነ፥ ለእ​ነ​ርሱ አሳ​ልፎ ሊሰ​ጠኝ ለማን ይቻ​ለ​ዋል? እኔ ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ብያ​ለሁ።” 12ከዚ​ህም በኋላ ፊስ​ጦስ ከአ​ማ​ካ​ሪ​ዎቹ ጋር ተማ​ክሮ፥ “ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ካልህ ወደ ቄሣር ትሄ​ዳ​ለህ” አለው።
ጳው​ሎስ በአ​ግ​ሪ​ጳና በበ​ር​ኒቄ ፊት ስለ መቅ​ረቡ
13ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ንጉሥ አግ​ሪ​ጳና በር​ኒቄ ወደ ቂሣ​ርያ ወር​ደው ፊስ​ጦ​ስን ተገ​ና​ኙት። 14በእ​ርሱ ዘንድ ብዙ ቀን ከቈዩ በኋላ ፊስ​ጦስ የጳ​ው​ሎ​ስን ነገር ለን​ጉሡ ነገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ፊል​ክስ በእ​ስር ቤት ትቶት የሄደ አንድ እስ​ረኛ ሰው በእ​ዚህ አለ። 15በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሳለ​ሁም ሊቃነ ካህ​ና​ትና የአ​ይ​ሁድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ እኔ መጥ​ተው እን​ድ​ፈ​ር​ድ​በት ማለ​ዱኝ። 16እኔም፦ ተከ​ሳሹ በከ​ሳ​ሾቹ ፊት ሳይ​ቆም፥ ለተ​ከ​ሰ​ሰ​በ​ትም ምላሽ ይሰጥ ዘንድ ፋንታ ሳያ​ገኝ ማንም ቢሆን አሳ​ልፎ መስ​ጠት የሮ​ማ​ው​ያን ሕግ አይ​ደ​ለም ብየ መለ​ስ​ሁ​ላ​ቸው። 17ከዚ​ህም በኋላ፤ በዚሁ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ ሳል​ዘ​ገይ በማ​ለዳ በፍ​ርድ ወን​በር ተቀ​ምጬ፥ ያን ሰው እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘ​ዝሁ። 18የከ​ሰ​ሱ​ትም በቆሙ ጊዜ፥ እኔ እንደ አሰ​ብ​ሁት በከ​ሰ​ሱት ክስ የሠ​ራው ምንም ነገር የለም። 19ስለ ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ቸው ከሆ​ነው ክር​ክ​ርና ስለ ሞተው፥ ጳው​ሎስ ግን ሕያው ነው ስለ​ሚ​ለው ሰው ስለ ኢየ​ሱስ ከሆ​ነው ክር​ክር በቀር፤ 20ስለ ክር​ክ​ራ​ቸ​ውም የማ​ደ​ር​ገ​ውን አጥቼ ጳው​ሎ​ስን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄደህ በዚያ ልት​ከ​ራ​ከር ትወ​ዳ​ለ​ህን? አል​ሁት። 21ጳው​ሎስ ግን እንቢ ብሎ፥ እን​ዲ​ድን ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ አለ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ቄሣር እስ​ክ​ል​ከው ድረስ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቁት አዘ​ዝሁ።” 22አግ​ሪ​ጳም ፊስ​ጦ​ስን፥ “እኔም ያን ሰው ልሰ​ማው እወ​ዳ​ለሁ” አለው፤ ፊስ​ጦ​ስም፥ “እን​ግ​ዲ​ያስ ነገ ትሰ​ማ​ዋ​ለህ” አለው።
23በማ​ግ​ሥ​ቱም አግ​ሪ​ጳና በር​ኒቄ በብዙ ግርማ መጡ፤ ከመ​ሳ​ፍ​ን​ቱና ከከ​ተ​ማው ታላ​ላቅ ሰዎች ጋርም ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስ​ጦ​ስም ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጡት አዘዘ። 24ፊስ​ጦ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ፥ እና​ን​ተም ከእኛ ጋር ያላ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሁላ​ችሁ፥ ስሙ፤ አይ​ሁድ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ እን​ዳ​ይ​ገ​ባው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆነ በዚህ እየ​ጮሁ የለ​መ​ኑኝ ይህ የም​ታ​ዩት ሰው እነሆ። 25እኔ ግን ለሞት የሚ​ያ​ደ​ር​ሰው በደል እን​ዳ​ል​ሠራ እጅግ መር​ምሬ፥ እር​ሱም ራሱ ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ማለ​ትን ስለ​ወ​ደደ እን​ግ​ዲህ ልል​ከው ቈር​ጫ​ለሁ። 26ነገር ግን ስለ እርሱ ወደ ጌታዬ የም​ጽ​ፈው የታ​ወቀ ነገር የለ​ኝም። ስለ​ዚህ ከተ​መ​ረ​መረ በኋላ የም​ጽ​ፈ​ውን አገኝ ዘንድ ወደ እና​ንተ ይል​ቁ​ንም ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ ወደ አንተ አመ​ጣ​ሁት። 27የበ​ደሉ ደብ​ዳቤ ሳይ​ኖር እስ​ረ​ኛን ወደ ንጉሥ መላክ አይ​ገ​ባ​ምና፤ ለእ​ኔም ነገ​ሩም ሆነ አስሮ መላኩ አስ​ቸ​ግ​ሮ​ኛል።”#“ለእ​ኔም ነገ​ሩም ሆነ አስሮ መላኩ አስ​ቸ​ግ​ሮ​ኛል” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 25